Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

ብጉር ህመም በቆዳ ላይ ያሉ ቀዳዳዎች ሲደፈኑ የሚፈጠር አነስተኛ እብጠት

ብጉርን እንዴት እንከላከል

 

Image result for ብጉር

 

ብጉር ህመም በቆዳ ላይ ያሉ ቀዳዳዎች ሲደፈኑ የሚፈጠር አነስተኛ እብጠት ነው፤ ጥናቶች እንደሚያስረዱትም በአለማችን ላይ ከሚከሰቱ የቆዳ ችግር ውስጥ ከፍተኛውን ድርሻ ይወስዳል፡፡

 

ብጉር እንዴት ይፈጠራል?

·   በቆዳ ላይ ያሉ ቀዳዳዎች ሲደፈኑ እና ከመደበኛው የቆዳ ሴል ቁጥር የበዛውን የቆዳ ሴል  ሴበም በተባለ ቆዳን ለማለስለስ የተዘጋጀ የሰውነት ውህድ በብዛት አምርቶ የቆዳን ቀዳዳን ሲዘጋ ህመሙ ይከሰታል፡፡

·   የቆዳን ወዝ አምጪ የሆነውን ሴበምን የሚያመርቱት ሰባሺየስ ግላንድስ(የላብ ከረጢቶቸ) በጉርምስና እና በወጣትነት ጊዜ በቁጥርም በመጠንም ከፍተኛ እድገት ስለሚኖራቸው፡፡ 

·   በመጠንና በብዛት የሚመረተው ሴበም ለባክቴሪያ እድገት ምቹ በመሆኑ፡፡

·   ባክቴሪያዎቹም በቆዳ ቀዳዳው አካባቢ መቆጣትን ሲያስከትሉ ነው፡፡

 

ብጉር አምጪ መንስኤዎች እነማን ናቸው?

·  የሆርሞን ለውጦች፡- በወጣትነት እድሜ ለዚህ አይነቱ የአንድሮጅን ሆርምን ለውጥ መከሰት በተለይ እስከ 30 እና 40ኛው እድሜ ድረስ ዋነኛው ምክንያት ነው፡፡

·  ቅባትነት ያላቸውን ኬሚካሎች በፊት ላይ ወይም ብጉር በሚወጣበት ቦታ ላይ መጠቀም ሌላኛው መንስኤ ነው፤ ብዙ ጊዜም ብጉር ለሚያጠቃቸው ሰዎች Water-based  እና non-comedogenic  የሚሉ ቅባቶችን በተለየ መልኩ መጠቀም የተሻለ ውጤት አሳይቷል፡፡

·  ፊትንም በሳሙና ደጋግሞ መታጠብ በቆዳ ላይ ያለውን ሴበምን ከመቀነስ ይልቅ ሙሉ በሙሉ በማጠፋት ፊትዎ እንዲደርቅ እና እንዲላላጥ በማድረግ ብጉርን ያባብሳሉ፡፡

·  የአምሮ ውጥረትና ጭንቀት ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ብጉርን እንዲባባስና ደጋግሞም እንዲከሰት ያደርጋሉ፡፡

 

ብጉርን እንዴት እንከላከል?

·  ፊቶትን በቀን ከሁለት ጊዜ በላይ አይታጠቡ፤ ሲታጠቡም በጣም ባልፈላ ለብ ያለ ውሃ ይጠቀሙ ከተቻለም የሳሙና ይዘታቸው አነስተኛ የሆኑ የብጉር ሳሙናዎችን ይጠቀሙ፡፡ Cetaphil®, Oil of Olay® ወይም Dove® ሳሙናዎችን በኛ ሃገር ተመራጭ ናቸው፡፡

·  ብጉርን በጣት መነካካትም የብጉሩ ቦታ ላይ ጠባሳ ከማሳረፉም አልፎ እብጠት እንዲፈጠር በማድረግ የመዳን ሂደቱን እንዲዘገይ ያረጋል፡፡

·  non-comedogenic የሆኑ ፊት ማለስለሻዎችን መጠቀም

·  አንዳንድ የብጉር አይነቶች ፀሃይ ብርሃን ሲያገኛቸው የመባስ ስሜት ይኖራቸዋል በዚህ ጊዜ በሃኪም የሚታዘዙ ሰን ስክሪኖችን እንዲጠቀሙ ይመከራል አልያም SPF 15 ወይም ከዚህ በላይ የሆኑ ሰን ስክሪኖችን ይጠቀሙ፡፡

·  ከላይ የተጠቀሱትን ጤና ምክሮች እየተጠቀሙ የቆዳ ሃኪምን ማማከር ውጤቱን ሙሉ በሙሉ ውጤታማ ያረገዋል እንላለን፡፡

 

ምንጭ፡-.ethiohakim