Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

ህጎች ከቦታ ቦታ እንዲሁም ከጊዜ ጊዜ እንደሚለያዩ ይታወቃል፡፡

ገራሚ ህጎች

 

ህጎች ከቦታ ቦታ እንዲሁም ከጊዜ ጊዜ እንደሚለያዩ ይታወቃል፡፡ በአንድ አካባቢ ትክክለኛ መስሎ የሚታየው ህግ በሌላ ቦታ አስቅኝ ወይም አስገራሚ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ በተጨማሪም በአንድ ወቅት ተገቢ ነው ብለን ያመንበት ህግ ሌላ ጊዜ ተገቢ ሳይሆን ይቀራል፡፡ ለዛሬ፤ ሳነብ ያገኘኋቸውንና እኔን ያስገረሙኝን 10 ህጎችን ከዚህ በታች አቅርቤላችኋለሁ፡፡

 

    1. ማስቲካ ማላመጥ በሲንጋፖር

ማስቲካ ማላመጥ ወደ እስር ቤት ሊያስወስደኝ ይችላል ብለው አስበው ያውቃሉ? እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ1992 በሲንካፖር ማስቲካ ማላመጥ ሙሉ ለሙሉ በህግ የተከለከለ ነው፡፡ በመሆኑም ወደ ሀገሪቱ ማስቲካ እንዳይገባ ተከልክሏል፡፡ ይሁንና ሲጋራን ለማቆም የሚረዳው የማስቲካ አይነት በሃኪም ከታዘዘ ግን ማስቲካ ማላመጥ ይፈቀዳል … እንደ መድሃኒትነት መሆኑ ነው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ  አንድ ሰው ማስቲካ መንገድ ላይ ተፍቶ ቢገኝ 500 የአሜሪካን ዶላር ቅጣት እንዲከፍል ይደረጋል፡፡

 

    1. ካልጠገቡ አይከፍሉም በዴንማርክ

ዴንማርክ በደስታ የተሞሉ ነዋሪዎች እንደዳለት ካሁን በፊት የአለም የደስተኝነት ደረጃን በተመለከተ ባቀረብኩት ጽሁፌ አይተናል፡፡ ደስተኛ ከሚያደርጓቸው ነገሮች አንዱ ይህ ህግ ሳይሆን አይቀርም፡፡ በዴንማርክ ሬስቶራንቶች ገብተው የሚመገቡ ከሆነና ምገቡ ካላጠገበዎ ሂሳብ ለመክፈል አይገደዱም እንዲሁ ሳይከፍሉ ከሬስቶራንቱ ውልቅ ማለት ይችላሉ፡፡

 

    1. መሞት የማይፈቀድበት ቦታ በብሪታኒያ

እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በብሪታኒያ አንድ ግለሰብ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት ወይም ፓርላማ ውስጥ መሞት አይፈቀድልትም ነበር፡፡ ምክርቤቱ ግቢ ውስጥ ሞቶ የተገኘ ሰው ንጉሳዊ የቀብር ስነ-ስርዓት ሊደረግለት ስለሚገባ ቅጥር ገቢው ውስጥ የታመመ ሰው ወይም ደከም ያለ ሰው ከታየ ወዲያዉኑ በጥበቃ ከግቢው እንዲወጣ ይደረግም ነበር፡፡

 

    1. ጋብቻና ዝምድና በዩታህ አሜሪካ

ከአሜሪካ ግዛቶች መካከል አንዷ የሆነችው ዩታህ ሁለት የቅርብ ዘመዶች መጋባት የሚያስችል ህግ አላት፡፡ ይህ ህግ ግን ተፈጻሚ የሚሆነው እድሚያቸው ከ65 አመት በላይ ለሆኑት ብቻ ነው፡፡

 

    1. ውፍረት በጃፓን

በጃፓን ሀገር አንድ ለየት ያለ ህግ አለ፡፡ እሱም ሜታቦ ህግ በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ ህግ ወፍራም መሆንን ይከለክላል፡፡ በዚህ ህግ መሰረት አንድ እድሜው 40ና ከዚያ በላይ ወንድ ጃፓናዊ የወገቡ መጠነ ዙሪያ ከ32 ኢንች መብለጥ እንደሌለበት የተደነገገ ሲሆን በተመሳሳይ መልኩ ለሴቶች ደግሞ ከ36 ኢንች በላይ እንዳይሆን ያስገድዳል፡፡

 

    1. ሴቶችና ሱሪ በፈረንሳይ

 

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1799 ከፖሊስ ለየት ያለ ፈቃድ ካላገኙ በስተቀር የፈረንሳይ ሴቶች  ሱሪ እንዲያደርጉ አይፈቀድም ነበር፡፡ በ1892 ሴቶች ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ሱሪ እንዲለብሱ በመፍቀድ ይህ ህግ ማሻሻያ የተደረገለት ነበር፡፡ በመቀጠልም በ1909 የፈረንሳይ ሴቶች ብስክሌት በሚጋልቡበት ወቅት ሱሪ እንዲለብሱ የሚፈቅድ የማሻሻያ ህግም ወጥቶ ነበር፡፡ ነገሩን ይበልጥ አስገራሚ የሚያደርገው  ግን ይህ 214 አመት ያስቆጠረው ህግ በ2013 ነበር ሙሉ ለሙሉ ከየተሰረዘው፡፡

 

    1. ዉሻና ቀልድ በኦክላህማ አሜሪካ

በአሜሪካዋ ግዛት በኦክላህማ በዉሻ ላይ መቀለድ በህግ ያስቀጣል፡፡ አንድ ሰው ወደ ዉሻ ጠጋ በማለት አስቂኝ ሆነ ፊት ለውሻው ቢያሳይ በእስር ወይም በገንዘብ ሊቀጣ እንደሚችል በህግ ተደንግጓል፡፡

 

    1. ሴቶችና መኪና በሳዉዲ

በአሁኑ ወቅት በአለማችን ሴቶች መኪና ማሽከርከር የማይችሉበት አገር ቢኖር ሳውዲ አረቢያ ውስጥ ብቻ ነው፡፡ በቅርቡ ይህ ህግ ሊቀየር እንደሚችል የሀገሪቱ ንጉስ አብደላ ፍንጭ አሳይተዋል፡፡

 

    1. የውስጥ ሱሪ በሚኒሶታ አሜሪካ

የአሜሪካ ግዛት በሆነችው ሚኒሶታ የሴትና የወንድ ውስጥ ሱሪን በአነድ የልብስ ማስጫ ገመድ ላይ ጎን ለጎን ማስጣት በህግ ያስጠይቃል፡፡

 

    1. ፍች በፊሊፒንስና ቫቲካን

በአለማችን መፋታት በህግ የተከለከለባቸው ሁለት አገራት ብቻ ናችው … ፊሊፒንስና ቫቲካን፡፡

 

 ምንጭ፡-proudlyhabesha.