Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

ማንኛውም ሰው ጤናማ ኑሮ መኖር ይችላል፡፡

ወደ ጤናማ ኑሮ ለመሸጋገር ፰ እርምጃዎች

 

ማንኛውም ሰው ጤናማ ኑሮ መኖር ይችላል፡፡ በእርግጥ ጤናማ ኑሮ በአንድ ጊዜ የሚገኝ ሳይሆን የረጅም ጊዜ ቁርጠኝነትን የሚጠይቅ ነገር ነው፡፡ ይሁንና ከትናንት ይልቅ ዛሬን ጤናማ ለማድረግ እንዲሁም ደግሞ የተሸለ ነገ እንዲኖረን ለማድረግ  መወሰድ ያለባቸው እርምጃዎች እንዳሉ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ ከዚህ በመቀጠል ጤናማ ኑሮን ለመኖር የሚነርዱንን ጠቃሚ ምክሮች በዝርዝር አስቀምጣለሁ፣

 

እርምጃ  ፩         ራስዎን የጤና ሁኔታ ይገምግሙ

ወደ ጤናማ ኑሮ ለመሸጋገር የሚረዳን የመጀመሪያው እርምጃ አሁን የሚገኙበትን የጤና ሁኔታ መገምገምና ማወቅ ነው፡፡ ማድረግ ከሚገባዎት መካከል፣

 

ከሐኪም ጋር በመሄድ የጤንነትዎን ሁኔታ ማወቅ

ቁመትዎን፣ ክብደትዎን፣ የወገብዎን መጠነ ዙሪያ በመለካትና የአካል መረጃ ጠቋሚ (BMI) በማስላት ምን ያህል ወፍራም እንደሆኑ ማወቅ

እንቅስቃሴን ገምግም ማለትም እርስዎ በአንድ ሳምንት ውስጥ ምን ያህል አካላዊ እንቅስቃሴ ያደርጋሉ? ምን አይነት እንቅስቃሴ ያደርጋሉ? እንቅስቃሴ ሲያደርጉ እርስዎ ምን ያህል ደስተኛ ይሆናሉ? አዋቂ ግለሰቦች በሳምንት ቢያንስ ሁለት ሰዓት ተኩል ቀለል መካከለኛ ጫና ኤሮቢክ እንቅስቃሴ ወይም አንድ ሰዓት ከሩብ ጠንከር ያለ ጫና ኤሮቢክ እና በሳምንት ቢያንስ ሁለት ቀናት ጡንቻ የሚያጠናክሩ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ እንዳለባቸው የጤና ባለሙያዎች ይመክራሉል፡፡

ስለተመገቡት ምግብ አይነትና መጠን በየለቱ ማስታወሻ የመያዝ ልምድ ማዳበር

ስሜታዊ ደህንነትንና ጉልበትዎን መገምገም

ማህበራዊ ግንኙነትዎን ይመልከቱ፡፡ ማለትም ቤተሰብ እና ጓደኞችዎ ጋር ያለዎት ግንኙነቶች ምን ያህል ጤናማ መገምገም

 

እርምጃ  ፪         ከጭስ ይራቁ

ሥር የሰደደ የጤና ችግር ማለትም የልብ በሽታ፣ የስኳር በሽታ፣ ጭንቀት፣ ወይም ሌሎች እንዳሉበዎ ከተረዱ ሲጋራ ማጨስን ጨምሮ ከማንኛዉም ዓይነት  አደገኛ ሱሶች ራሳዎን ማራቅ ይኖርብዎታል፡፡ እነዚህን ችግሮች ለመፍታት አንድ ግለሰብ ብቻውን የሚያደርገው ተግባር አይደለም፡፡ ሥለሆነም ከሐኪምዎ ጋር መነጋገር የግድ ይላል፡፡

 

እርምጃ ፫          በይበልጥ ይንቀሳቀሱ

በየጊዜው የሚያደርጉትን በተቻለ መጠን አዝናኝ ለማድረግ ይሞክሩ፡፡ ለምሳሌ ከጓደኞችዎ ጋር በመሆን የእግር ጉዞ ቢጓዙ፤ ተራራ መውጣት ባህልን ቢያዳብሩ፤ የዳንስ ወይም የካራቴ ትምህርት ቢወስዱ አዝናኝ የሆነ ነገር ሊያግኙ ይችላሉ፡፡

 

እርምጃ  ፬        አመጋገብዎን ያሻሽሉ

የተሻለና ጤናማ ኑሮ ለመኖር ቀጣዩ እርምጃ አመጋገብ ማስተካከል ነው፡፡ አመጋገብን ለማስተካከል በመጀመሪያ አስተሳሰባችንን ማስተካከል እነደሚጠበቅብን የስነ-ምግብ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ ለምሳሌ “አትክልትና ፍራፍሬ መመገብ አለብኝ” ብሎ ከማሰብ ይልቅ “አትክልትና ፍራፍሬ መመገብብ እመርጣለሁ” ብሎ ማሰብ የተሻለ ነው፡፡ ምክንያቱም ይህ አይነት አገላለጽ እርስዎ እየወሰዷቸው ባሉት እርምጃዎች ቀጥተኛ ተሳታፊ እንደሆኑና በምርጫዎ እንጂ በግዳጅ እያደረጉት አለመሆኑ ስለሚያሳይ ነው፡፡

 

ለአመጋገባዎ እቅድ ያውጡ፡   በጣም እስኪርበን ድረስ መጠበቅ ተገቢ አይደለም ምክንያቱም በጣም የተራቡ ግለሰቦች ሰላጣና የመሳሰሉት የምግብ አይነቶችን ከመመገብ ይልቅ ወደ ስጋ ነክ ምግቦች ስለሚሳቡ ነው፡፡

ፍጥነትዎን በመቀነስ ምግብዎን ያጣጥሙ፡ ምግብ በሚመገቡበት ወቅት ቴሌቪዥን አይመልከቱ ሌላ ሥራም አይስሩ፡፡

የተለያዩ ፍራፍሬዎችንና አትክልቶችን ይመገቡ፡ አቅምዎ በፈቀደው መጠን በየዕለቱ የተለያዩ ፍራፍሬዎችንና አትክልቶችን መመገብ ተገቢ ነው፡፡ በአንድ ቀን ውስጥ ከአምስት እስከ ዘጠኝ የሚደርሱ የተለያዩ ፍራፍሬዎችንና አትክልቶችን መመገብ እርስዎ የሚያስፈልግዎን ሁሉ ንጥረ ነገሮች ለማግኘት ይረዳዎታል፡፡

 

እርምጃ ፭           ጭንቀትን ይቀንሱ

የተሻለ ህይወት እንዲኖረን ከውጥረት የጸዳ ኑሮን መምራት ይኖርብናል፡፡ 

የሚያስጨንቅ ነገር ሲያጋጥምዎ “ይህ ነገር ከጥቂት ጊዜ በኋላም የኔው ጉዳይ ሆኖ ይቆያል ወይ?” ብለው ራስዎን ይጠይቁ፡፡ መልሱ “አይ አይቆይም” የሚል ከሆን ስለምን ራስዎን ያስጨንቃሉ ታዲያ፡፡

ጭንቀት ከሚያመጡ ሃሳቦች ይልቅ ቀና ስለሆኑ ነገሮችንና ሰዎችን ያስቡ

በረጅሙ ይተንፍሱ

 

እርምጃ  ፮          የተሻለ እንቅልፍ ይተኙ

የእንቅልፍ ችግር ካለብዎ፣ እነዚህን ጠቃሚ ምክሮች ይሞክሩ፡

ከመተኛትዎ ከሁለት ሰዓታት በፊት ከቴሌቪዥንና ከኮምፒውተር መራቅ፣

የመኝታ ሰዓት በቀረበ ጊዜ ከባድ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግ፣

ሞቅ ባለ ዉሃ ሰዉነትን መታጠብ

የማነቃቃት አቅም የሌላቸውን ትኩስ ነገሮች መጠጣት

መደበኛ እንቅልፍ ፕሮግራም ማዘጋጀት

 

እርምጃ ፯      ማህበራዊ ግንኙነትዎን ያሻሽሉ

የአመጋገብ ለውትና እንቅስቃሴ በማድረግ ብቻ ጤናማ ኑሮ ሊኖረን ይችላል ብሎ ማሰቡ አስቸጋሪ ነው፡፡ ስለሆነም እርስዎ ከሌሎች ሰዎች ጋር ያለዎት ግንኙነት መሻሻል አለበት፡፡ የእርስዎን ማህበራዊ አውታረ-መረብ ለማስፋት እነዚህን ጠቃሚ ምክሮች ይመልከቱ፡

ከእርስዎ ተመሳሳይ የሆነ አስተሳሰብ ካላቸው ሰዎች ጋር የቅርብ ወዳጅነት ይመስርቱ

ሰዎች ​​ጋር ጥሩ ጊዜ ያሳልፉ.

ማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይም ሆነ በአካል (የፊት-ለፊት) ግንኙነት ይገንቡ

የፍቅር ግንኙነትዎን በተመለከተ እገዛን ባሰፈለገዎ ጊዜ የሌሎችን እገዛ ይጠይቁ

 

እርምጃ  ፰       አእምሮዎን ዘወትር ያሰሩት

ሌሎች ሰዎች ጋር በመሆን አእምሮን የሚያነቃቁ እንቅስቃሴዎች ላይ መሳተፍ ለአንጎል ጥሩ እንደሆነ ባለሞያዎች ይስማሙበታል፡፡ አእምሮን በሚያነቃቁ ሥራዎች ላይ የተሰማሩ ሰዎች በመርሳት በሽታ የመጋለጥ እድላቸው

 

ምንጭ፡-proudlyhabesha.