Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

የተለያዩ አይነት የጎመን ዝርያዎች ያሉ ሲሆን ሁሉም በቫይታሚን ኤ፤ ሲ፤ካ

ጎመን ለጤና

 

በአገራችን ከተዘወተሩት አባባሎች መካከል “ጎመን በጤና” የሚለው አንዱ ይሁን እንጅ ጎመን ለጤና የሚለው አባባል እንብዛም አይታወቅም:: የዛሬው ርዕሳችን የአረንጓዴ ተክሎች ለጤና የሚያበረክቱት ጠቃሜታ  ላይ የሚያተኩር ይሆናል … ጎመን ለጤና፡፡ ስለሆነም የአረንጓዴ ተክል አይነቶችና  የጤና በረከቶቻቸዉን በጥቂቱ ከዚህ በመቀጠል እናያለን፡፡

 

ሠላጣ (salata)

ሠላጣን መመገብ ለደም ግፊት ህመምተኞችና ከፍተኛ የሠዉነት ክብደት ላላቸዉ ሠዎች የሚመከር ሲሆን የደም ዉስጥ ስር መጠንንም ይቀንሳል፡፡ ሠላጣ በዉስጡ የያዘዉ ካልሲየምና ፎስፈረስ ለአጥንት ጤናማነት ጠቃሚ ሲሆን ሴሊኒየም የሚባለዉ ንጥረ ነገር ደግሞ የሠዉነታችን ቆዳ ቶሎ እንዳረጅና የአንጀት ካንሠርን የመከላከል አቅም እንዲኖረዉ ያደርጋል፡፡

 

የጀርመን ሰላጣ

የጀርመን ሰላጣ ሠዉነታችንን ካንሰር እንዲዋጋ አቅም የሚሠጥ ሲሆን ከዛም ባለፈ ለብጉር፤የፀጉር መነቀል እና ሌሎችንም ይከላከላል፡፡

 

ቆስጣ (black cabbage)

ቆስጣን መመገብ የጉበት፣ የአንጀት፣ የማህፀን እና የፕሮስቴት ካንሰር ተጋላጭነትን እንደሚቀንስ ጥናቶች የሚያሳዩ ሲሆን ከነዚህም በተጨማሪ ለጡንቻ መዳበር ጠቃሚነት አለዉ፡፡

 

ብሮኮሊ(brocolli)

ይህ አትክልት በቫይታሚን ሲ እና በፋይበር የበለጸገ ሲሆን በዉስጡ የያዛቸዉ ንጥረ ነገሮች በሽታን የመከላከል አቅማቸዉ ከፍተኛ ነዉ፡፡ የሳንባ እና የካንሰር ህመሞችን የመከላከል አቅም አለዉ፡፡

 

ጥቅል ጎመን (cabbage)

የተለያዩ አይነት የጎመን ዝርያዎች ያሉ ሲሆን ሁሉም በቫይታሚን ኤ፤ ሲ፤ካልሲየም እና ሌሎች ንጥረ ነገሮች የበለጸጉ ናቸዉ፡፡በአዉስትራሊያ የተሰራ ጥናት እንደሚያመለክተዉ እነዚህን አረንዴ ተክሎች መመገብ ለካንሰር ተጋላጭነትን ይቀንሳል፡፡

 

የሾርባ ቅጠል(Spinach) 

ምግብን ለማጣፈጥ የምንጠቀምበት የሾርባ ቅጠል በዉስጡ ፎሊክ አሲድ፣ቫይታሚን ኤ፣ቢ፣ኬ እና ሌሎች ንጥረ ነገሮችን የያዘ ሲሆን የአጥንት መሳሳትንና የልብ ህመም ተጋላጭነትን እንደሚቀንስም ጥናቶች ያሳያሉ፡፡

 

ጥቁር ጎመን

ጥቁር ጎመን በዉስጡ ቫይታሚን ቢ1፣ቢ2፣ቢ3፣ቢ6 ፣ሲ እና ሌሎች እንደ ፖታሲየም ፣ካልሲየም ፣ፎስፈረስ እና አዮዲንንም ይይዛል፡፡የሠዉነት የበሽታ የመከላከል አቅምን የሚያጠነክርና በሽታንም የሚከላከል የተክል አይነት ነዉ፡፡

 

 ምንጭ፡-proudlyhabesha.