ለሰፊ ያመረቀዘ ቁስል (ቃጠሎ፣ ቁስል፣ ወዘተ) የሚጠቅሙ የቤት ውስጥ መፍት
የፓፓያ ወተት መሰል ፈሣሽ እና የበሰለ ፓፓያ
-
- ያልበሰለውን ፓፓያ ፍሣሽ ለመውሰድ በመጀመሪያ ፓፓያውን በተፈላ ውሃ በደንብ ማጠብና መቁረጥ።
- ከዚያም ነጩን ፈሣሽ በንፁህ ማንኪያ ወይም ስኒ ማጠራቀም።
- አንድ ሊትር ተፈልቶ የቀዘቀዘ ውሃ ላይ ከ3 - 5 ጠብታ የፓፓያ ፍሣሽ አድርጎ ማደባለቅ።
- በተዘጋጀው የውሃና የፓፓያ ፍሣሽ ቅልቅል ቁስሉን ሦስት ጊዜ ማጠብ (ቁስሉን ለማጠብ እንደ አማራጭ የጨው እና ሙቅ ውሃ ቅልቅል መውሰድ ይቻላል)።
- ከዚያ ሊበስል ያለውን ፓፓያ ፈጭተው በቁስሉ ላይ ማድረግ (ቁስሉ በጣም ያልመረቀዘ ከሆነ ፓፓያው ያልበሰለ መሆን ይገባዋል)።
- ይህንንም ዘዴ ጥዋት፣ ከሰዓትና ምሽት ላይ መደጋገም።
ምንጭ
የተፈጥሮ መድኃኒት ሕክምና በምድር ወገብ ሞቃታማ አካባቢ (በዶ/ር ዲቴር ሹሞል ፤ ትርጉም:- በተሾመ ነጋሽ ካሣየ )
Related Topics