ጉንፋን በህመሙ በተጠቁ ሰዎች አማካኝነት አልያም ደግሞ በመጥፎ ሽታ እና

የጉንፋንን መዛመት ለማስቆም የሚረዱ መንገዶች

 

Image result for ጉንፋን

 

ጉንፋን በህመሙ በተጠቁ ሰዎች አማካኝነት አልያም ደግሞ በመጥፎ ሽታ እና በአየር መበከል ምክንያት እንደሚከሰት ይነገራል።

ታዲያ ይህ የተለመደው እና ትንሽ ምቾት የሚነሳው የጉንፋን ህመም ጥንቃቄ እንደሚያስፈልገውም ነው ባለሙያዎች የሚናገሩት።

ብዙ ጊዜ ለዚህ ህመም መከላከያ ተብለው ከሚመከሩት መንገዶች ባለፈ ግን ጤናማ ሊባል የሚችል የአኗኗር ዘይቤ መከተል መልካም መሆኑንም ይመክራሉ።

የአሜሪካ በሽታ መከላከያና መቆጣጠሪያ ተቋም ደግሞ የዚህን ህመም ስርጭት ለመከላከልና ለመቆጣጠር ያስፈልጋሉ ያላቸውን ዘዴዎች ጠቅሷል።

ተቋሙ ስርጭቱን ለመከላከል ከህክምናው ባሻገር በተያዘው ግለሰብ መደረግ አለባቸው ያላቸውን ምክረ ሃሳቦች ነው ያስቀመጠው።

በተቻለ መጠን በህመሙ ከተያዙ ሰዎች መራቅ፦ ይህን በማድረግ በንክኪ ከሚመጣ የጉንፋን ቫይረስ መተላለፍ ራስዎን ይታደጋሉ።

ጉንፋን ከያዘዎት ከቤት አይውጡ ምክንያቱም ከዕረፍት ማነስ ቶሎ አያገግሙም አልያም ህመሙን ወደ ሌሎች ሰዎች ሊያዛምቱ ይችላሉና ነው።

ሲስሉም ሆነ ሲያስነጥሱ በተቻለ መጠን አፍና አፍንጫዎን በመሃረብ እና በሶፍት ነገር ይሸፍኑ።

ሁልጊዜም ቢሆን እጅን በውሃና በሳሙና በደንብ ይታጠቡ፥ ሳሙና የማያገኙ ከሆነ አልኮል ነክ ማጽጃዎችን ተጠቅመው ለብ ባለ ውሃ እጅዎን ይለቃለቁ።

ጉንፋን ተይዘውም ሆነ ሳይያዙ አፍ፣ አፍንጫና አይንዎን መነካካት ያቁሙ።

ዘወትር ቤትዎን፣ ተማሪ ከሆኑ መማሪያ ክፍል ውስጥ አልያም የስራ ቦታ የሚጠቀሙባቸውን መሳሪያዎችና የሚቀመጡበትን ስፍራ ንጹህ እና ፅዱ ለማድረግ ይሞክሩ።

 

ሳል እና የተቆራረጠ እንቅልፍ ስለሚኖር እረፍት ወስደው ረዘም ላለ ጊዜ እስከሚሻልዎት ድረስ ለመተኛት ይሞክሩ።

የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ያዘውትሩ፥ ይህን ከቻሉ ሳይታመሙ ቢያደርጉት ይመረጣል ካልሆነ ግን ጉንፋኑ ከተሻለዎት በኋላ ዳግም ላለመጠቃት ይረዳዎታል።

አለመጨናነቅ እና ራስን ነጻ ማድረግ ከዚህ ባለፈም አልኮል ነክ ያልሆኑ ፈሳሾችን አብዝቶ መጠቀምም ሌላው አማራጭ ነው።

የተመጣጠነ እና ለሰውነትዎ ተስማሚ የሆነ አመጋገብ ቢከተሉ ደግሞ መልካም ነው ይላል የተቋሙ ምክረ ሃሳብ።

እነዚህ የጉንፋንን ስርጭት ለመከላከልም ሆነ ከተያዙ በኋላ በፍጥነት ለማገገም ይረዳሉ ተብለው በተቋሙ የተቀመጡ ምክረ ሃሳቦች ናቸው።

ምንጭ፦ www.upi.com/

 

  

Related Topics