በዚህም ፀሀይ በብዛት የምትወጣባቸው ወቅቶች ላይ የሰዎች የአእምሮ ጤንነ

የፀሀይ ብርሃን እና የአእምሮ ጤና ግንኙነት…

 

የፀሀይ ብርሃን ከአእምሮ ጋር ግንኙነት እንዳለው አዲስ የወጣ ጥናት አመልክቷል።

የአሜሪካው ብሪንግሃም ያንግ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች እንዳስታወቁት፥ የፀሀይ ብርሃን በአጠቃላይ ጤንነታችን ላይም ይሁን በአእምሮ ጤና ላይ ከፍተኛ ሚና አለው።

እንደ ተመራማሪዎቹ፥ የፀሀይ ብርሃን በሚቀንስባቸው ወቅቶች የአእምሮ ጤና መዛባት እና ለጭንቀት የመጋለጥ እድል በብዛት የሚከሰቱባቸው ናቸው፤ በፀሀያማ ወቅቶች ደግሞ የአእምሮ ጤንነት መሻሻል የሚያሳይበት ጊዜ ነው ብለዋል።

እንዲህ አይነት ችግሮች ከአየር ፀባይ መለዋወጥ ጋር ተያይዞ የጤና እክል ለሚያጋጥማቸው ሰዎች ብቻ ሳይሆን፥ በሁሉም ሰዎች ላይ ሊከሰት የሚችል ነው ብለዋል።

በፀሀይ ብርሃን እና በአእምሮ ጤና መካካል ያለውን ግንኙነት ለመለየትም ሶስት ተመራማሪዎች በየፊናቸው ያገኙትን መረጃ አንድ ላይ በማድረግ ጥናት አካሂደዋል።

ጥናቱ የአየር ፀባይ ተለዋዋጭነትን ከግምት ውስጥ በማስገባት የተካሄደ መሆኑም ተገልጿል።

በዚህም ፀሀይ በብዛት የምትወጣባቸው ወቅቶች ላይ የሰዎች የአእምሮ ጤንነት እና የጭንቀት ደረጃ የቀነሰ መሆኑን ተለይቷል።

ከፍተኛ መጠን ያለው የፀሀይ ብርሃን በሚወጣባቸው ቀናቶች አልፎ አልፎ ደመና ቢታጀቡም እንኳ ለጤንነታችን በጎ ጎን እንዳለው ነው ተመራማሪዎች የተናገሩት።

በተቃራኒው ዝናባማ እና ደመናማ የሆነ አየር በሚስተዋልበት ወቅት የሰዎች አእምሮ ለጭንቀት የተጋለጠ ነው፤ ይህ ደግሞ በአጠቃላይ ጤንነት ላይም ይሁን አእምሮ ላይ ጉዳት ያደርሳል ሲሉም ተመራማሪዎቹ አብራርተዋል።

አሁን ይፋ የተደረገው ጥናት በፀሀይ ብርሃን እና በእምሮ ጤና መሃል ያለውን ግንኙነት እንጂ ምክንያቱ ምንድነው በሚለው ላይ ምንም ያስቀመጠው ነገር የለም።

ሆኖም ግን ከዚህ ቀደም የተሰራ ጥናት እንደሚያመለክተው፥ ከፀሃይ ብርሃን እንደሚገኝ የሚነገረውና በውስጣችን ያለ የቪታሚን D መጠን የአእምሯችን ጤንነት ላይ ተፅእኖ እንዳለው ያመለክታል።

የኢራኑ ኢፍሻን ሜዲካል ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ያወጣው ሪፖርት እንዳመለከተው፥ የቪታሚን D እጥረት ያላቸው ሰዎች፤ በቂ የቪታሚን D መጠን ካላቸው ጋር ሲነፃፀር፥ አነስተኛ መጠን ያቸው ሰዎች የአእምሮ ጤንነት ዝቅተኛ ሆኖ መመዝገቡ ይታወሳል።

 

ምንጭ፦ www.huffingtonpost.co.uk

 

  

Related Topics