በዓለም ዙሪያ የሰው ልጅ በተለያየ አይነት የካንሰር ህመም አይነት መጠቃት

የአፍ ካንሰርና መንስዔዎቹ...

 

 

በዓለም ዙሪያ የሰው ልጅ በተለያየ አይነት የካንሰር ህመም አይነት መጠቃት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል።

ከነዚህ የካንሰር አይነቶችው ውስጥ ደግሞ እምብዛም ተነግሮለት የማያውቀው የአፍ ካንሰር አንዱ ነው።

በብዛት ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን ባለመከተል የሚከሰተው የአፍ ካንሰር፤ ከ20 ዓመታት ወዲህ የተጠቂዎች ቁጥር በሁለት ሶስተኛ እየጨመረ መምጣቱ ነው የሚነገረው።

የእንግሊዝ የካንሰር ማእከል ያወጣው መረጃ የአፍ ካንሰር ተጠቂዎች መጠን በ68 በመቶ መጨመሩን የሚያመለክት ሲሆን፥ በሁሉም የእድሜ ክልል ላይ የሚገኙ ሴቶችን እና ወንዶችን እንደሚያጠቃም ያመለክታል።

መረጃው በእንግሊዝ ብቻ በየዓመቱ 11 ሺህ 400 ሰዎች በአፍ ካንሰር ይጠቃሉ የሚል ሲሆን፥ ከነዚህም ውስጥ የከንፈር፣ የምላስ፣ የቶንሲል እና የጉሮሮ የማህልኛው ክፍል ካንሰር ይገኙበታል።

በአፍ ካንሰር ምክንያትም በሀገሪቱ በዓመት 2 ሺህ 300 ሰዎች ህይተዋቸው እንደሚያልፍም ነው የተነገረው።

 

የአፍ ካንሰር መንስዔ…

ለአፍ ካንሰር ከሚዳርጉን ነገሮች ውስጥ ዋነኛው እና ቀዳሚው የአኗኗር ዘይቤያችን ነው የተባለ ሲሆን፥ ጤናማ ያልሆነ የአኗኗር ዘይቤን የማይከተሉ ሰዎች የበለጠ ተጋላጭ ናቸው ብለዋል።

ተመራማሪዎች ለአፍ ካንሰር መንስኤ የሆኑትን ለመለየት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጣር ከ1993 እስከ 1995 እንዲሁም ከ2012 እስከ 2014 በ100 ሺህ ሰዎች ላይ ጥናት ያደረጉ ሲሆን፥ ለአፍ ካንሰር ዋነኛ መንስኤ ናቸው የተባሉትንም መለየት ችለዋል።

ከነዚህም ውስጥ፦

ሲጋራ ማጨስ፦ እንደ ተመራማሪዎቹ ከገለጻ 65 ከመቶው የአፍ ካንሰር ሲጋራ ከማጨስ ጋር ተያይዞ ነው የሚከሰተው ይላሉ።

አልኮል መጠጣት፦ አልኮልን አዘውትረው የሚጠጡ ሰዎችም 13 በመቶ ለአፍ ካንሰር ተጋላጭ ናቸው ይላሉ ተመራማሪዎቹ።

አመጋገብ፦ የአመጋገብ ስርዓታችን ጤናማ እና ያልተመጣጠነ ከሆነም ለአፍ ካንሰር ተጋላጭ መሆናችንንም ተመራማሪዎቹ ያብራራሉ።

 

የአፍ ካንሰር ምልክቶች…

ምላሳችን አካባቢ ወይም አፋችን ውስጥ ለረጅም ጊዜ የቆየ የህመም ስሜት፣ በከንፈራችን ላይ ወይም በአፋችን የውስጠኛው ክፍል ላይ ማበጥ፣ በአፋችን ውስጥ ቀይ ወይም ቀይና ነጭ ምልክቶች እንዲሁም አንገታችን አካባቢ ምንነቱ ያልታወቀ እብጠት ምልክቱ ናቸው እና ችላ ሊባል አይገባም ብለዋል።

 

የአፍ ካንሰርን ለመከላከል…

የአፍ ካንሰርን ለመከላለክ ከሚመከሩ ተግባራት ውስጥ ከቃሚው ጤናማ የሆነ የአኗኗር ዘይቤን መከተል ነው።

እንዲሁም ሲጋራ አለማጨስ፣ የአልኮል አወሳሰዳችንን መቀነስ እንዲሁም በእለት ተእለት ምግባችን ውስጥ አትክልት እና ፍራፍሬን ማካተት የአፍ ካንሰር ተጋላጭነትን ለመቀነስ ይረዳል።

ምንጭ፦ www.dailymail.co.uk

 

  

Related Topics