የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጤናማ እና በስፖርት የተገነባ ሰውነት ይኖር ዘን

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለአዕምሮ ጤና

 

Image result for የአካል ብቃት እንቅስቃሴ

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጤናማ እና በስፖርት የተገነባ ሰውነት ይኖር ዘንድ ያስችላል።

በየዕለቱ የሚደረግ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ደግሞ በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች እንዳሉት ይነገራል።

በኋለኛው የእድሜ ክልል በጤና ለመኖር እና ተደጋጋሚ የህክምና ክትትልን ለማስወገድ በወጣትነት ዘመን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግን የህክምና ባለሙያዎች ይመክራሉ።

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለአዕምሮ ጤና፤

ለማገናዘብ አቅም፦ እንቅስቃሴ ማድረግ ሰውነት የተሻለ እንዲለጠጥ እና በሰውነት ውስጥ የኦክስጅን መንሸራሸርን ይጨምራል።

ይህ ደግሞ በአዕምሮ ውስጥ የተሻለ የደም መፍሰስ እንዲኖር በማድረግ በእድሜ መግፋት የሚመጣ የማገናዘብ አቅም ማነስን ማስወገድ ያስችላል።

በዚህ ረገድ እድሜያቸው ከ60 እስከ 70 አመት የሚደርሱ አረጋውያን የአካል ብቃት እንቅስቃሴን እንዲያደርጉ ይመከራል።

በአዕምሮ ውስጥ ያሉ ሆርሞኖችን ለማሳደግ፦ ምግብ ለሰውነት እንደሚያስፈልገው ሁሉ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አዕምሮ ውስጥ ያሉ ሴሎችም እንዲበዙ እና እንዲያድጉ ይረዳል ይላሉ ባለሙያዎች።

ይህም አብዝተው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ባደረጉ ቁጥር ለማስታወስ እና ነገሮችን ለመገንዘብ የሚረዳውን የአዕምሮ ክፍል የሚቆጣጠረውን ሆርሞን በብዛት ማመንጨት ይችላሉ።

ይህ ሲሆን ደግሞ የአዕምሮ የማገናዘብ አቅም እጅጉን ይጨምራልና ሰውነትዎን እየገነቡ አዕምሮዎን ያዳብሩ።

ጭንቀትና ድብርትን ለማስወገድ፦ ድብርት የአዕምሮን ብቃት የመቀነስ እና ብሎም የማጥፋት ሃይሉ ከፍተኛ ነው።

ድብርት በተያዙ ጊዜ ነገሮችን አገናዝቦና አስተውሎ ለመረዳት እና ለመመለስ ይቸገራሉ፤ በዚህ ምክንያትም አላስፈላጊ ውሳኔ ሊወስኑም ይችላሉ።

ሃኪም ቤት መሄዱ ጊዜያዊ መፍትሄ እንጅ ዘላቂ መፍትሄ አያመጣም የሚሉት ባለሙያዎች፥ ይህ ነገር ከቆየ ወደ በሽታነት ተቀይሮ በመድሃኒት መንቀሳቀስን ብቻ እንደሚያስከትልም ይገልጻሉ።

እናም ሲጀመር ከባድ ቢመስልም ዘወትር የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ብቻ እንደ መፍትሄ ይጠቀሙ ሲሉም ይመክራሉ።

ይህን ሲያደርጉ አዕምሮ የደስታ እና የፈንጠዝያ ስሜት የሚያመጡትን ሴሮቶኒን እና ዶፓሚን የተባሉ ሆርሞንችን በብዛት እንዲያመነጭ ያደርገዋል።

እነዚህ ሆርሞኖች ደግሞ ሃዘን የሌለበት የደስታ ስሜትን ማጣጣም የሚያስችለውን ኢንዶርፒንስን መጠን በመጨመር ከድብርት ስሜት ለመላቀቅ ይረዳወታል።

የድካም ስሜትን ለመቀነስ፦ ሌላው ጠቀሜታው ደግሞ ድካም እና በድካም ምክንያት የሚፈጠር የሰውነት መልፈስፈስን ለመቀነስ ነው።

በሰውነት ውስጥ የኮርቲሶልን መጠን መቀነስ እና አዳዲስ ሴሎችን ማመንጨትም የዚሁ አካል ነው፤ ይህ ደግሞ ለሰውነት ብርታትና ንቃት እንደሚረዳ ነው ባለሙያዎች የሚናገሩት።

የአዕምሮን ብቃት ከፍ ለማድረግ፦ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ አዕምሮ በጣም ውስብስብ የሆኑ ነገሮችን ለመፍታት የሚያስችለውን አቅም ይበልጥ እንዲያዳብር ይረዳዋል።

ይህን ሁኔታም ባደረግነው ምርመር አረጋግጠናል ነው የሚሉት ባለሙያዎቹ፤ እንደ እነርሱ ገለጻ በእንቅስቃሴ ምክንያት አዕምሮ በጣም ውስብስብ የሆኑ ቀመሮችን እና የተለየ የማሰብ ችሎታ የሚጠይቁ ጉዳዮችን መፍታት የሚያስችለውን አቅም ይገነባል።

 

የበሽታ ተጋላጭ እንዳይሆኑ ቅድመ ጥንቃቄ፦ በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ወቅት አዕምሮ በስኳር እና ቅባት በበዛባቸው ምግቦች ሳቢያ የሚመጣን በሽታ ቀድሞ የመለየት አቅምን ያዳብራል።

ይህም እንደ ስኳር የመሳሰሉ በሽታ ተጋላጭነትን ቀድሞ በመለየት ሰውነት የሚወስደውን የስኳር መጠን በመወሰን የተሻለ በሽታ የመከላከል አቅምን ያዳብራል።

በርካታ ጠቀሜታ ያለውን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግን ያዘውትሩና ጤንነትዎን ይጠብቁ መልዕክታቸው ነው።

ምንጭ፦ www.rd.com/

 

 

  

Related Topics