የቡና ዱቄት አይን ቆዳ ላይ ለሚወጣ ምልክት ፈውስነት

የቡና ዱቄት አይን ቆዳ ላይ ለሚወጣ ምልክት ፈውስነት

 

አንዳንድ ጊዜ ባልታሰበ ሁኔታ የሰውነት ቆዳ ላይ እንግዳ ነገር ሊመለከቱ ይችላሉ።

እነዚህ ነገሮች የቆዳ መቆጣት፣ መቅላት፣ አላስፈላጊ መስመሮች፣ የቆዳ መሸብሸብ፣ ጥቁር መስመርና የመብለዝ ምልክቶች ሊሆኑ ይችላሉ።

ከዚህ ባለፈም ጉንጭ ላይ የሚወጡ ክብ ምልክቶች ቀይ የቆዳ ላይ ነጠብጣቦችም ከዚህ ውስጥ ይመደባሉ።

ለእነዚህ ነገሮች ደግሞ የተለያዩ መፍትሄዎችን ይሞክራሉ፤ በህክምናም ይሁን በቤት ውስጥ በቀላሉ በሚዘጋጁ ውህዶች።

ከዚህ ውስጥ በአይን ቆዳ ላይ የሚወጣን ጥቁር ምልክት፣ መብለዝ እና የመሸብሸብ ችግር በቀላሉ ማከሚያ መንገዶችን ይመልከቱ።

በአይን ቆዳ የታችኛው ክፍል ላይ የሚወጣው ይህ ምልክት፥ የታችኛውን ቆዳ በጣም የማቅላትና የማበለዝ እንዲሁም የማጥቆር ሃይሉ ከፍተኛ ነው።

ከዚህ ባለፈም በእርጅና የሚከሰትን የቆዳ መሸብሸብን በአጋጣሚ ሊያስከትልም ይችላል።

ታዲያ ለዚህ ችግር ሁለት ውህዶችን ብቻ በመጠቀም በቀላሉ ማከም ይችላሉ።

የሚያስፈልጉ ነገሮች፦ በደንብ የላመ 1 የሾርባ ማንኪያ የቡና ዱቄት፣ 1 የሻይ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ 1 የሻይ ማንኪያ የፓልም ዘይት።

አዘገጃጀት፦ ውህዶችን በሻይ ማንኪያ ውሃ በደንብ ማዋሃድና መቀላቀል።

ከዚያም የአይን የታችኛው ቆዳ ላይ ሌላ ቦታ ሳያስነኩ መቀባት እና ከ5 እስከ 10 ደቂቃ ባለበት ማቆየት።

በኋላ በንጹህ ፎጣ በመጥረግ ለብ ባለ ውሃ መለቃለቅ።ወይም ደግሞ የቡናውን ዱቄት ብቻውን ሳይቀጥን በውሃ መለወስ እና ማዘጋጀት።

ይህንንም በጥንቃቄ አይን እንዳይነካ አድርጎ የሁለቱንም አይን የታችኛውን ቆዳ መቀባትና ከ10 እስከ 15 ደቂቃ ማቆየት።

ከተባለው ጊዜ በኋላ በንጹህ ፎጣ ጠርጎ ለብ ባለ ውሃ መታጠብ፤ ሁለቱንም ድግግሞሽ በሳምንት ለ2 ወይም 3 ቀናት ማድረግ።

ቁንዶ በርበሬው በደም ውስጥ ለሚኖረው የኦክስጅንና የንጥረ ነገሮች ዝውውር በእጅጉ ይረዳል።

አጠቃላይ ውህዱ ደግሞ ምልክቱ ያለበት አካባቢ የሚከሰተውን የማቃጠልና የመለብለብ ስሜትንም ያስወግዳል።

ይህ ምልክት እንዳይስፋፋና የረጅም ጊዜ ችግር እንዳይሆን ማድረግም ሌላው ጠቀሜታው ነውና በተመቸዎት መንገድ ይሞክሩት።

ምንጭ  (ኤፍ ቢ ሲ)

 

  

Related Topics