ዋትስአፕ በ1 ወር ጊዜ ውስጥ አገልግሎት የሚያቋርጥባቸው ስልኮች የትኞቹ

ዋትስአፕ በ1 ወር ጊዜ ውስጥ አገልግሎት የሚያቋርጥባቸው ስልኮች የትኞቹ ናቸው…?

 

 

የማህበራዊ ትስስር ድረ ገጽ የሆነው እና በርካታ ተጠቃሚዎች ያሉት ዋትስአፕ ቀደም ባሉ ጊዜያት በተመረቱ ስልኮች ላይ የምሰጠውን አገልግሎት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር የ2016 ማገባደጃ ላይ አቋርጣለው ማለቱ ይታወሳል።

እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር የ2016 የመጨረሻ ወር መግባቱን ተከትሎም በሚሊየን የሚቆጠሩ ስማርት ስልኮች ላይ የዋትሳፕ አገልግሎት እንደሚቋረጥ እየተጠበቀ ነው።

በአሁኑ ጊዜ በዓለም ዙሪያ በቢሊየን የሚቆጠሩ ተጠቃሚዎች እንዳሉት የሚታወቀው ዋትስአፕ፥ ቀደም ባሉ ጊዜያት በተመረቱ ስልኮች ላይ አገለግሎቱን የማቋርጠው የምሰጠውን አገልግሎት የበለጠ አመቺ ለማድረግ ነው ሲልም አስታውቋል።

ዋትስአፕ አገልግሎት የሚያቋርጥባቸው የስማርት ስልክ አይነቶች…

ለአይፎን ተጠቃሚዎች

ዋትሳፕ በዚህ ወር ውስጥ አይፎን 3GS በሚባሉት እና እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጣር በ2009 ለገበያ በቀረቡት ስማርት ስልኮች ላይ አገልግሎቱን ሙሉ በሙሉ ያቆማል ተብሏል።

ከዚህ በተጨማሪም የአይፎን ኦፕሬቲንግ ሲስተም የሆነውን iOS 6 በሚጠቀሙ ስማርት ስልኮች ላይም አገልግሎቱ እንደሚቋረጥ ነው ዋትስአፕ ያስታወቀው።

ይህ ማለትም ወደ iOS 9.3 አፕዴት ያልተደረጉ አይፎን 4፣ 4s ወይም 5’ን ሊያካትት እንደሚችል ነው የወጡ መረጃዎች የሚያመለክቱት።

እንዲሁም ፈርስት፣ ሰከንድ፣ ሰርድ እና ፎርዝ ጄኔሬሽን በመባል የሚታወቁት የአፕል አይፓድ ምርቶችም አገልግሎቱ ከሚቋረጥባቸው ውስጥ ይገኛሉ።

ታዲያ አገልግሎታችሁ እንዳይቋረጥባችሁ ከፈለጋችሁ የአይ.ኦ.ኤስ ኦፕሬቲንግ ሲስተማችሁን አፕዴት መሆን አለመሆኑን ሴቲንግ ውስጥ በመግባት ወደ ጄነራል ሴቲንግ ከገባን በኋላ ሶፍትዌር አፕዴት የሚለው ውስጥ ገብተን ማረጋገጥ እንችላለን።

 

ለአንድሮይድ ተጠቃሚዎች

አንድሮይድ 2.1 ወይም 2.2 ቨርዥን የሚጠቀም ማንኛውም ስማርት ስልክ እና ታብሌት ላይ በመገባደድ ላይ በሚገኘው የፈረንጆቹ 2016 የዋትሳፕ አገልግሎት ይቋረጣል ተብሏል።

ይህም እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጣር በ2010 እና በ2011 መካከል በማንኛውም አምራች የተመረቱ አንድሮይድ ስማርት ስልኮች እና ታብሌቶችን ያካትታል።

አገልግሎቱ እንዳይቋረጥባችሁ ከፈለጋችሁ ወደ ሴቲንግ በመግባት የትኛውን የአንድሮይድ ቨርዥን እንደምትተቀሙ በማየት ማሻሻል ካለባችሁም አሻሽሉ ተብሏል።

 

ለዊንዶውስ ስልክ ተጠቃሚዎች…

ከዊንዶውስ ስማርት ስልኮች ውስጥ ዊንዶስው ፎን 7 የዋትስ አፕ አገልግሎት ከሚቋረጥበት ውስጥ ይገኝበታል።

 

ለኖኪያ እና ብላክቤሪ ተጠቃሚዎች…

ዋትስአፕ በብላክቤሪ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ላይ አገልግሎቱን ያቋርጣል፤ እንዲሁም በብላክ ቤሪ 10፣ ኖኪያ S40 እና ኖኪያ ሲምባያን S60 ስልኮች ላይ አገልግሎታቸው ይቋረጣል ተብሏል።

እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2017 ዋትስአፕን መጠቀም የምትፈልጉ ከሆነ የስልካችሁን ኦፕሬቲንግ ሲስተም አፕዴት ማድረግ ወይም አዲስ ስልክ መቀየር የግድ እንደሆነም ነው የተገለፀው።

 

ምንጭ፦ www.mirror.co.uk/tech

 

  

Related Topics