በቅርቡ በጥናታዊ ምርምር የተገኙ ቦርጭን ለማጥፋት የሚጠቅሙ የምግብ አይ

ቦርጭን የሚያጠፉ ምግቦች

ቦርጭን የሚያጠፉ ምግቦች

 

 በቅርቡ በጥናታዊ ምርምር የተገኙ ቦርጭን ለማጥፋት የሚጠቅሙ የምግብ አይነቶችን ዘርዝሯል።

እነዚህ የምግብ አይነቶች ጠቃሚ በመሆናቸውም ልናካፍላችሁ ወደድን።

1. ጭማቂዎች
ከተለያዩ ፍራፍሬዎች የሚሰሩ ጭማቂዎች ለጤና ጠቃሚ የሆነ የቅባት አይነት ስላላቸው ከመጠን ያለፈ ቦርጭን ይከላከላሉ። ጭማቂዎቹን ሲያዘጋጁ ስኳር ባይጨምሩ ይመከራል።

2. እንቁላል
በእንቁላል ውስጥ የሚገኝ ኮሊን የሚባል ንጥረ ነገር ስብን የሚያስከትሉ ጂኖችን እንደሚያጠፋ ተመራማሪዎች ይናገራሉ በመሆኑም ለቁርስ ተመራጭ ምግብ ነው።

3. ቀያይ ፍራፍሬዎች
እንደ ፓም እና እንጆሪ ያሉ ፍራፍሬዎች ለጤና ጠቃሚ ሲሆኑ በአጠቃላይ ደማቅ ቀለም ያላቸው ፍራፍሬዎች ቦርጭን የሚያመጡ ጂኖችን የማስቆም አቅም እንዳላቸው ነው በጥናቱ የተረጋገጠው።

4. የወይራ ዘይት
ወይራ ዘይት በውስጡ የያዘው የቅባት አይነት ፣ ርሀብን እስከ አራት ሰዓት በማስታገስ አቅሙና ለጤና እጅግ ተስማሚ በመሆኑ ለቦርጭ እንዳንጋለጥ ያደርጋል።

5.ሩዝ ባቄላ እና አጃ
እነዚህ ምግቦች በአንጀት ውስጥ ከሚገኙ ባክቴሪያዎች ጋር በመሆን ለስኳር ህመም የሚያጋልጡ ጂኖችን ማስቆም የሚችሉ ሲሆን፥ አጃን ለቁርስ መመገብ ለጤና እጅግ ጠቃሚ እንደሆነ በጥናቱ ተገልጿል፤ የሚመገቡት የሩዝ አይነት ከተገኘ ቡኒ ሩዝ ቢሆን ይመረጣል።

6.በፕሮቲን የበለፀጉ ምግቦች
እንደ አደንጓሬ አተር እና ለውዝ ያሉ ጥራጥሬዎችን መመገብ ቦርጭን ለመከላከል እንደሚረዳ ተመራማሪዎቹ ይናገራሉ።

7.አረንጓዴ ተክሎች
በእለት ተዕለት የምግብ አመጋገብ ፕሮግራማችን ውስጥ አረንጓዴ ተክሎችን ማካተት በቅባት ብዛት ስብ በሰውነታችን እንዳይከማች ያደርጋል።

8.አረንጓዴ ሻይ

አረንጓዴ ሻይን መጠጣት የተከማቸ ስብ እንዳይኖር ስለሚያስችል ቦርጭ እንዳይከሰት ይከላከላል።

 ምንጭ፡-በዶ/ር ሆንለያት

 

 

  

Related Topics