የእረፍት ቀናችንን የተሻለ እንዲሆኑ የሚረዱ ነጥቦች

 

ሳምንቱ የእረፍት ቀናት

ብዙዎቻችን ከሳምንቱ የእረፍት ቀናት ተመልሰን ሰኞ ወደመደበኛ ስራ ስንመለስ ሰላታ መለዋወጣችን እና እረፍት እዴት ነበር መባባላችን የተለመደ ነው፤ ምንም እኳን አሁን አሁን ቅዳሜ እና እሁድ በስራ ማሳለፍ የተለመደ እየሆነ ቢመጣም፡፡ ይሁንና ከአጠቃቀማችን እና ከሚያጋጥሙን ነገሮች የተነሳ ለአንዳንዶቻችን አጭር ለሌሎች ደግሞ ረጅም ፤ ለተቀረውም መልካም እና አስደሳች ሊባል ይችላል፡፡ ከዚህ በመነሳት የእረፍት ቀናችንን የተሻለ እንዲሆኑ የሚረዱ ነጥቦችን ቀጥሎ አቅረብንላችኋል፡፡ መልካም ንባብ፡፡

1-      አርብን አይዘንጉ፤ ምንም እኳን በስራ ተወጥው ቆይተው በቅዳሜ እና እሁድ ማረፍ ከፈለጉ ከአርብ መጀመርን አይርሱ፡፡ አርብ ከስራ መልስ ቀለል ያሉ እና ዘናሊያደርግዎት የሚችል ነገርን መርጠው ይተግብሩ፡፡ ለምሳሌ ከቤተሰብ ጋር መሆን፤ ፊልሞችን መመልከት፤ እና ቀለል ያለ የእግር ጉዞ በማድግ እና አእምሮዎን በማሳረፍ ይጀምሩ፡፡

2-     የመኝታ ሰአትዎን በእረፍት ቀናት እና በስራ ቀናት መካከል ሰፊ ልዩነት ያለው አያድርጉ፤ ቅዳሜ እና እሁድ ከለመድነው ሰአት ሰፊ ልዩነት ያለው እንቅልፍ የምንተኛ ከሆነ ያለንን የእረፍት ቀን ከሚበቃን በላይ በመተኛት ከማባከናችን በላይ ወጥ የሆነ ንቁ የመሆን ሁኔታችንን ሊያዛባ ይችላል፡፡

3-     የሚያዝናናዎትን ነገር ይምረጡ፤ የእረፍት ቀንዎን በዘፈቀደ በመባከን ላለማሳለፍ ሊያዝናናዎት እና አእምሮዎን ይበልጥ ንቁ የሚደርግዎትን ነገር መርጠው ይተግብሩ፡፡ ለምሳሌ የስፖርት ጫወታን መከታተል፤ ከሚወዱት ሰው ጋር ጊዜን ማሳለፍ / አብሮ መመገብ / ወይም ለብቻ መመሰጥና የእግር ጉዞ ማድረግ ሊሆን ይችላል፡፡

 

4-    በሳምንቱ መጨረሻ ሁሌ የሚከውኑትን አዝናኝ ነገር መርጠው ልምድዎ ያድርጉ፤ ይህም ትኩረትዎንና አእምሮዎን ሳምንቱን ሙሉ ሲያስቡት ከከረሙት ነገር ነጻ በማውጣት ለመዝናናት እና ለመታደስ ዝግጁነትን ያፋጥናል፡፡ ይህም መነቃቃትዎን በመጨመር የእረፍት ቀንዎን ከስራ ቀንዎ ጋር ተጣምሮ ተናፋቂ እዲሆን ያደርገዋል፡፡

 

5-     ትኩረትዎን በእረፍትዎ ላይ ያድርጉ እንጂ ስለሚቀጥለው ሰኞ በመጨነቅ/በማሰብ ትኩረቶን በታትነው ባታደሰ መንፈስ እና አእምሮ ወድስራ እዳይመለሱ፡፡ ይህም በአንዳዶች ከሰኞ ምሽት የሚጀምር መሸበርን የሚያካትት ሲሆን በማግስቱ ወደስራ በሚመለሱበት ሰአት አያብሰለሰሉ በመቆየትዎ ዝለትን ያመጣብዎታል፡፡

መልካም የእረፍት ቀን!    

Source: www.happier.com