ጥፍራችን ስለ ጤናችን እንደሚናገር ያውቃሉ

ጥፍራችን ስለ ጤናችን እንደሚናገር ያውቃሉ?

 
ጥፍራችን ስለ ጤናችን እንደሚናገር ያውቃሉ?
 

 የጥፍራችን ቀለም፣ ቅርፅና ስፋት ለተለያዩ የጤና ችግሮች መጋለጣቸውን እንደሚያሳዩ ተገለጸ።

ከዚህ በታች በምስል ተደግፈው በምናያቸው ነጥቦች ጥፍሮቻችን ለአደገኛ በሽታ መጋለጣችንን ሊያሳዩ እንደሚችሉ እንመለከታለን።

የጥፍር ቀለም መለዋወጥ፣ መቆሸሽና መወፈር ሰውነታችን እክል እንዳጋጠመው የሚያሳዩ ማስጠንቀቂያ ደወል ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል።

1.    የጥፍር ቀለም

የጤናማ ጥፍር ቀለም ወደ ሮዝ እና ነጭ ያጋደለ ሲሆን መብቀያው (ስሩ) ነጭ የጨረቃ ቅርጽ ይይዛል። 

አረንጓዴ ቀለም ያለው ጥፍር የባክቴሪያ ኢንፌክሽን ምልክት ነው። 

በጥፍሮቻችን ላይ ቀያይ መስመሮች ከታየቱም ከልብ በሽታ ጋር የተያያዘ ችግር እንዳለብን ያመላክታሉ።

ሰማያዊ ጥፍሮችም ደማችን ኦክስጅን በበቂ ሁኔታ እያገኘ አለመሆኑን ሊያሳዩ ይችላሉ ነው የተባለው።

ነጭ ቀለም ያላቸው ጥፍሮችም ከጉበት ጋር የተያያዘ ችግር እንዳለብን የሚያስጠነቅቁ ሲሆን በጥፍሮቻችን የላይኛው ክፍል የሚታዩ ጥቋቁር ነጥቦች ደግሞ የእድሜ መግፋትን ያመላክታሉ።

nail_green.jpg

2. ወፍራም ጥፍሮች

ወፍራም ጥፍሮች በተፈጥሮ የሚከሰቱ ወይም የተለመዱ አይደሉም፤ ከሳንባ እና ተያያዥ በሽታዎች ጋር ይያያዛሉ እንጂ። 

ወፍራምና የተቦረቦሩ ጥፍሮች እድገትን የሚቆጣጠር እጢ በሽታ እና መሰል ችግሮች ምልክት ሊሆን እንደሚችሉም ይነገራል።

ወፍራም ጥፍሮች የደካማ ደም ዝውውር ውጤት መሆናቸውም ተደርሶበታል።

thick-nails.jpg

3. የተሰነጣጠቁ ጥፍሮች 

ጥፍሮች የሚሰነጣጠቁት የፎሊክ አሲድ፣ ቫይታሚን ሲ እና ፕሮቲን እጥረት ነው። 

በጥፍራችን ስሮች ላይ የሚታዩ ነጭ ነጥቦች 10 በመቶ ለሚሆነው የሚያሳክክ የቆዳ በሽታ መነሻ ናቸው።

የተሰነጣጠቁ ጥፍሮች ብዙ ጊዜ ስር ከሰደደ የምግብ እጥረት ጋር የሚያያዙ ናቸው።

4. ወደ ውጪ የሚታጠፉ ጥፍሮች

ጥፍራችሁ ወደ ውጪ የሚታጠፍና የማንኪያ ቅርጽ የሚሰራ ከሆነ እንዲሁም በጣም ስስ ከሆነ የብረት ንጥረ ነገር እጥረት ወይም ብዛት አልያም የልብ ህመም ምልክት ሊሆን ይችላል።

5. የተቦረቦሩ ጥፍሮች

የተቦረቦሩ ጥፍሮች ለሚያሳክክ የቆዳ በሽታ አልያም ጸጉርን ለሚጨርስ በሽታ መጋለጥን ያመለክታሉ።

ምንጭ፦ http://www.healthylifetricks.com

 

 

  

Related Topics