በአንድሮይድ ስልካችን ላይ ያሉ የግል ፋይሎችን ሌሎች ሰዎች እንዳያዩብን

በአንድሮይድ ስልካችን ላይ ያሉ የግል ፋይሎችን ሌሎች ሰዎች እንዳያዩብን ለማድረግ

 

በስማርት ስልኮች ላይ ፎቶግራፎችና ቪዲዮዎችን እንዲሁም የተለያዩ የግል ፋይሎችን ይዘን ስንቀሳቀስ እንስተዋላለን። በስማርት ስልኮች ላይ ፎቶግራፎችና ቪዲዮዎችን እንዲሁም የተለያዩ የግል ፋይሎችን ይዘን ስንቀሳቀስ እንስተዋላለን። ታዲያ ስልካችንን ባጋጣሚ ለሰው በምንሰጥበት ጊዜ የሰጠነው ወይም ደግሞ አስቀምጠን ያገኝው ሰው በስልኩ ውስጥ ያሉ ፋይሎችን እንዳያዩብን እና ስልካችንን በነጻነት ለሰዎች እንድንሰጥ የሚያስችሉንን መንገዶች እንጠቁማችሁ።ፋይል መቆለፊያ /File locker/ የፋይል መቆለፊያ / File locker/ መተግበሪያ በስልካችን ላይ የያዝናቸው መረጃዎቻችን በሌች ሰዎች በቀላሉ እንዳያዩብን ከሚያደርጉ ዘዴዎች አንዱ ነው።ይህም መተግበሪያው ባለው የፋይል ማናጀር አማካኝነት የግል ፋይሎቻችንን፣ ፎቶግራፎች ወይም ቪዲዎች ያሉበትን ፎልደር በመምረጥ በይለፍ ቃል ወይም ፓዎርድ ለመቆለፍ የሚያስችል ነው።

 

ይህንን መተግበሪያ ከጎግልፕሌይ / Google play store/ ዳወንሎድ በማድረግ መጠቀም የምንችል ሲሆን፥ ተጥቃሚዎች ይህንን መተግበሪያ በሚጠቀሙበት ጊዜ ልብ ሊሉት ይገባል የተባለው ነገር የምንሰጠው የይለፍ ቃል ወይም ፓስዋርድ በቀላሉ የሚያዝ መሆን አለበት ተብሏል ምክንያቱ ደግሞ የይለፍ ቃሉን አንዴ ከረሳን ፋይሎቻችንን ከፍተን ለማየት የምንችልበት አማራጭ ባለመኖሩ ነው። የምስል መደበቂያ መተግበሪያ /Hide pictures- keep safe vault/ይህ የምስል መደበቂያ / Hide pictures- keep safe vault/ መተግበሪያ በአንድሮይድ ስልኮቻችን ላይ ያሉን ፎቶግራፍ እና የተንቀሳቃሽ ምስሎች በሌሎች ሰዎች እንዳይታዩብን ለማድረግ የሚረዳን መተግበሪያ ነው። ይህንን መተግበሪያ ለመጠቀምም እንዳይታዩብን የምንፈልጋቸውን ምስሎች ከከፈትን በኋላ ኪፕ ሴፍ/‘keep safe’/ የሚለው ላይ ሼር በማድረግ ምስሎቹን ከሌሎች ሰዎች እይታ መሰወር እንችላለን።

 

ይህንን መተግበሪያ ስልካችን ላይ በማውረድም በስልኮቻችን ላይ ያሉንን ግላዊ ሚስጥሮች መጠበቅ እንችላለን። lፋይሎቻችን ስም በምንሰጥበት ወቅት ከፊትለፊቱ ነጥብ (.) ማስገባት ይህ መንገድ ቀላሉ እና ሌላ ተጨማሪ መተግበሪያ ሳያስፈልገን በስልካችን አንዲሮይድ ፋይል ማናጀር በመጠቀም ፋይሎቻችንን ሌሎች ሰዎች እንዳያዩብን የሚያደርግልን ነው። ይህንን ለመጠቀምም በስልካችን ላይ ሴቭ የምናደርገውን ፋይል ስም ከመስጠታችን በፊት ከፊት ለፊቱ ነጥብ (.) አስቀድመን በማስገባት ስሙን ጽፈን ሴቭ ማድረግ ነው።

 

በዚህ መንገድ ሴቭ ያደረግናቸው ፋይሎች በቀላሉ ፊት ለፊት ላይ ለሌሎች ሰዎች አይታዩም። እነዚህን ፋይሎች መልሰን በራሳችን ጊዜ ከፍተን ማየት ከፈለግንም ፋይል ማናጀር ውስጥ ከገባን በኋላ ሴቲንጉን በመክፈት ከሚመጡልን ዝርዝሮች ውስጥ የተደበቁ ፋይሎችን ለመክፈት የሚረዳንን /show hidden files/ ከከፈትን በኋላ በሚመጣለን ስፍራ ላይ ነጥብን በማሰቀደም የሰጠነውን ስም አስገብተን በመጻፍ መመልከት እንችላለን።

ምንጭ፦ www.droidjar.com/

 

  

Related Topics