ሎሚ ለደማቅ የፀጉር ቀለም፣ለፎረፎር፣.ለጥፍር ጥንካሬና ለሌሎችም

 

ሎሚ ለደማቅ የፀጉር ቀለም፣ለፎረፎር፣.ለጥፍር ጥንካሬና ለሌሎችም……

 

ሎሚ በቫይታሚን ሲ ይዘቱ እጅግ የበለፀገ ፍራፍሬ ሲሆን፥ ለሰውነታችን ውስጣዊ ጤንነት እና ውጫዊ ውበት ጠቃሚ መሆኑ በስፋት ይነገርለታል።

ሎሚ በተጨማሪም እንደ ካልሺየም፣ ማግኒዢየም፣ ፖታሺየም እና ለበርካታ ሚንራሎች መገኛ ከመሆኑም ባሻገር ቆዳችን፣ ፀጉራችን እና ጥፍራችን ውብ ገፅታን እንዲላበስ የሚያደርጉ አንቲኦክሲዳንትስ በበቂ መጠን ይዟል።

 

ሎሚ ከምግብነት ባለፈ ለውበት ከሚያበረክታቸው አስተዋፅኦች ከብዙ በጥቂቱ እናስቃኝዎ፦

 

1.ብጉርና ጥቋቁር ነጠብጣቦችን ለማስወገድ፣

የብጉር ምስል ውጤት

 የሎሚ ተፈጥራዊ ፀረ ባክቴሪያ እና ፀረ ፈንገስ ባህሪ የፊት ገፅታንውብ እና ማራኪ ለማድረግ ተመራጭ ያደርገዋል።

 በመሆኑም አንድ ሎሚ ወስደን  በመቆራራጥ በፊት ቆዳችን ላይ ማዳረስ፣ ከተቻላ ጥቂት ጠብታ ማር እየቀላቀሉ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ይህንኑ ማድረግ ከአምስት እስከ 10 ደቂቃ ይህን ካከናወንን በኋላ ቀዝቀዝ ባለ ውሃ መታጠብ።

 

2.ፈካ ያለ ፊት እንዲኖረን፣

የከንፈር ምስል ውጤት

 ሎሚ በአደጋ ምክንያት ለተከሰቱ ጠባሳ ምልክቶች ፣ ማድያት፣ የመበለዝ ምልክቶችን ለማጥፋት ያግዛል።

 በሎሚ ጭማቂ ውስጥ የሚገኘው ሲትሪክ አሲድ ቆዳችን ፈካ እና ቀላ እንዲል ከማድረጉም በላይ በቆዳ ላይ የሚታዩና የቆዳን ውበት የሚያበላሹ ምልክቶች እንዲወገዱ ያደርጋል።

 ይሁንና ሎሚን በተሰነጠቀ አና በቆሰለ ቆዳ ላይ መቀባት ከፍተኛ የማቃጠል ስሜት ሊያስከትልብን ስለሚችል ጥንቃቄ ሊወሰድ ይገባል።

 

3.ለነጣ ጥርስ፣

የጥርስ ምስል ውጤት

 ለፕሮፌሽናል የጥርስ ማፅጃዎች የምናባክነውን ከፍተኛ ወጪ በቤት ውስጥ ከሎሚ በምናዘጋጀው የጥርስ ማፅጃ ዘዴ በመተካት ወጪያችንን በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ እንችላለን።

 ቤኪንግ ሶዳ እና የሎሚ ጭማቂን በሚገባ በማዋሃድ በጥርስ መቦረሻ ወይም መሰል ነገር ከአንድ ደቂቃ ላለበለጠ ጊዜ በጥርሳችን ሁሉ ማዳረስ ከዚያም የጥርስ መቦረሻውን በውሃ እያራስን ቀስ በቀስ መለቃለቅ።

 

 

4.ወዛም ቆዳን ለማስተካከል፣

የወዛም ቆዳ ምስል ውጤት

 የአንዳንዶቻችን  ቆዳ በተፈጥሮ  ደረቅ ሲሆን፥ የአንዳንዶቻችን ደግሞ ወዛም ነው፤ ሁለቱም የቆዳ አይነቶች ግን የተመጣጠነ የቆዳ እንክብካቤን ይሻሉ። በመሆኑም ወዛም ቆዳን በተፈሮ የታደልን ሰዎች ወዛምነቱን በተወሰነ ደረጃ በመቀነስ ውብ የፊት ቆዳን ለመጎናፀፍ የሎሚ ጭማቂ ፍቱን ነው።

 ከመተኛታችን በፊት የሎሚ ጭማቂ ተቀብተን በማግስቱ መለቃለቅም ይህን ጥቅም በቀላሉ ያስገኝልናል።

 

5.ለደማቅ የፀጉር ቀለም፣

የከንፈር ምስል ውጤት

 ፀጉራችንን በምንታጠብበት ወቅት የሎሚ ጭማቂን እና የፀጉር ኮንዲሽነርን ከቀላቀልን በኋላ ፀጉራችን ላይ ማዳረስ፣ ከዚያም በደንብ ማበጠር ፣ በመቀጠል ከ20 እስከ 30 ደቂቃ ፀሃይ ካስመታነው በኋላ መለቃለቅ ።

 ይህንንም ቢያንስ በሳምንት አንድ ጊዜ ለአንድ ወር  ማድረግ፤ ውጤቱን ከወር በኋላ ያዩታል።

 

6.ለጥፍር ጥንካሬ፣

የከንፈር ምስል ውጤት

 ከገበያ የጥፍር ማጠንከሪያ ለማግኘት ሰፊ አማራጭ ሊኖርዎት ይችላለል ነገር ግን ከጥፍር ማጠንከሪያዎቹ የሚያገኙትን ጥቅም በቀላሉ ከሎሚም ማግኘት ይችላሉ።

 የሎሚ ጭማቂ እና የወይራ ዘይትን በመቀላቀል ጥፍራቸንን በየጊዜው መቀባቱ ለጥፍር ጥንካሬ ብቻ ሳይሆን ጥፍር ነጭ እና ውብ እንዲሆን ማድረግም ይቻላል።

 

7.ለፎረፎር፣

የፎሮፎር ምስል ውጤት

 ማር እና የሎሚ ጭማቂን ቀላቅሎ ለፀጉር መጠቀም ፎሮፎር እና የራስ ቅል ድርቀትን ለማስወገድ እጅግ ተመራጭ ነው።

 ይህን ቢያንስ በሳምንት ሁለት ጊዜ ተግባራዊ በማድረግ ውጤቱን ማግኘት ይቻላል።

 

8.ለተሰነጣጠቁ ከንፈሮች፣

የከንፈር ምስል ውጤት

 አንድ ሎሚ ወስደን በመቁረጥ ከመተኛታችን በፊት  ከንፈሮቻችንን በደንብ መቀባት በማግስቱ በቀዝቃዛ ውሃ መለቅለቅ ብቻ በቂ ነው።

 ይህም የሞቱ ሴሎችን በማንሳት በምትኩ ለስላሳ ከንፈር እንዲኖረን ያሰችላል።

ምንጭ፦ http://www.huffingtonpost.com