መረጃ ማነፍነፊያ (Search Engine)

 

Internet and websites

ለዓለማችን ህዝቦች ኢንተርኔትን እጅግ አስፈላጊና መሰረታዊ ጥያቄ ከሆነ ውሎ አድሯል፡፡ ይህም “መረጃ” ምን ያህል በማኅበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ እና በቴክኖሎጂያዊ መስኮች ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት የሚያሳይ ነው ። የሃገራት እድገትም ባለቸው የመረጃ ክምችት ተፅዕኖ ስር ወድቋል፡፡ የመረጃ ማህበረሰብ የሚለው ፅንሰ ሃሳብ ማቆጥቆም ከዚሁ ጋር ቀጥተኛ ዝምድና ያለው ሲሆን ሃገራትም ይህን ማህበረሰብ ከመፍጠር አንፃርም ከፍተኛ መዋለ ንዋይ በማፍሰስ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ የተለያዮ ፀሃፍት የመረጃ ማህበረሰብ በተለያ መልክ ተርጉመውታል፡ ለምሳሌ ፡- ማርቲን የሚባለው ፀሃፊ የመረጃ ማህበረሰብ ማለት የኑሮ ደረጃው ፣የለተለት ስራው፣ ትምህርቱ፣ የንግድ ስርዓቱ ወዘተ… ወቅታዊና በተሟላ መረጃ አቅርቦት ተፅዕኖ ስር የወደቀ በሚል ይገልፀዋል፡፡ ታዲያ ይህን ማህበረሰብ ለመፍጠር ኢንተርኔት እንደ ቁልፍ መሳሪያ ነው ፡ ኢንተርኔት አለምን ወደ አንድ መንደርነት ያቀራረበየመረጃ መለዋወጫ መረብ ነው፡፡

በአለማችን ላይ 500 ሚሊዮን የሚያህል ህዝብ የኢንተርኔት ተጠቃሚ ሲሆን 80 ፐርሰንት ያህል ተጠቃሚዎቹ ከበለፀጉ ሃገራት ናቸው፡፡ በማደግ ላይ ካሉ ሃገራት ሃገራት ከአጠቃላይ ማህበረሰቡ 2 ፐርሰንት ያህሉ ኢንተርኔት ተጠቃሚ እንደሆነ ይነገራል (ራኦ 2006 እ.ዮ.አ)፡፡ መረጃ ማነፍነፊያ (Search Engine) አይ ሲቲ 2 በዚህ ፅሁፍ ላይ ከበይነ መረብ (ኢንተርኔት) ላይ መረጃን ለማግኘት የሚረዳን ዋነኛና መሰረታዊ የሆነው መረጃ ማነፍነፊያ (Search Engine) ምንነት፣ አስፈላጊነት፣ እንዴት ስራውን እንደሚከውን እና ለኢትዮጲያ ስለሚኖረው ፋይዳ እንዳስሳለን። በአሁኑ ሰዓት እጅግ በርካታ የሆኑ ድረ-ገፆች በበይነ መረብ ላይ ይገኛሉ።

 

Hawassa Articles

ፋክት ሀንት እንዳወጣው ዘገባ እስከ 2013(እ.ዮ.አ) 759 ሚሊዮን ድረ-ገፆች ይገኛሉ።መረጃ ማነፍነፊያ (ሰርች ኢንጂን) በኢንተርኔት አማካኝነት በአለማችን ከሚገኙ መካነ ድሮች ላይ መረጃዎችን በማነፍነፍ፣ በማደራጀት ለተጠቃሚዎች ተደራሽ ማድረግ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ነው፡፡ ይህ ቴክኖሎጂ ምጡቅ ቀመርን (አድቫንስድ አልጎሪዝም) የሚጠቀም ሲሆን ተፈላጊና መረጃዎችና የመረብ አድራሻዎችን በፈጣን ሰዓት ውስጥ ይጠቁማል፡፡ መረጃ ማነፍነፊያ በተለያየ መልኩ ጥቅም ላይ የሚውል ሲሆን ራሱን ችሎ እንደ ማነፍነፊያ መጠቀምና አንዳንድ መካነ- ድሮች ደግሞ የራሳቸው የሆነ አነስተኛና በውስጣች የሚገኘውን መረጃዎችን ብቻ  የሚያፈላልጉበት ነው። ይህም የድረ- ገፁን ጎብኚዎች ቃላትን ወይንም ሀረግን ከድረ-ገፁ ፈልጎ ለማግኘት ይረዳል። መረጃ አነፍናፊዎች ስራቸውን እንዴት እንደሚከውኑና ከጀርባ ያሉትን ቴክኒኮች እንቃኛለን። የበይነ መረብ መረጃ አነፍናፊ ሦስት ዋና ዋና ደረጃዎች ያሉት ሲሆን እነዚህም ዌብ ክራውሊንግ፣ ዌብ ኢንዴክሲንግ እና ሰርቺንግ (መረጃ አሰሳ) የሰኛሉ፡፡

 

1. ዌብ ክሮሊንግ:

ክሮለር ወይም ስፓይደር የሚባለው የኮምፒዉተር ፕሮግራም ሲሆን ስራውም በበይነ መረብ ላይ ያሉ ገፆችን መጠቆም(locating)፣ማዉጣትና(fetching) ማስቀመጥ(storing) ነው። ዌብ ክሮለር ስለድረ ገፁ እና ስለ ማስፈንጠሪያዎች(links) መረጃዎችን ይሰበስባል።በዋናነት የሚከተሉትን መረጃዎችን ይመዘግባል።

• የድረ-ገፅ አድራሻ

• የገፁን ስም

• የድረ-ገፁን ሜታ ታግ

• በገፁ የተካተቱ ሌሎች መረጃዎች(Web page content)

• ገፁ ላይ የሰፈሩ ገፅ ማገናኛዎች( links) እና ወዴት

እንደሚመሩ መዝግቦ ይይዛል

 

2. ዌብ ኢንዴክሲንግ፡

ኢንዴክሲንግ የመረጃ ማነፍነፊያው ቁልፍ ሲሆን ከመረጃ ቋት ውስጥ መረጃዎች የሚገኙበትን አድራሻ ያመላክታል ። ዌብ ኢንዴክሰር

ለመረጃ ጥቆማ (ኢንዴክሲንግ) የሚረዱ መረጃዎችን ከክሮውለሩ በመጠቀም በድረ-ገፁ ውስጥ የሚገኙትን ቃላትና ሌሎች  ክመንቶች (እንደ pdf, word ... የመሳሰሉትን) በመረጃ ቋት ውስጥ ያስቀምጣል። በ‘Worldwidewebsize.com’ እንዳወጣው መረጃ ከሆነ ጎግል ብቻ እስከ 2014 ከ45 እስከ 50 ሚሊዮን የሚጠጉ ድረ-ገፆችን ኢንዴክስ አድርጓል።

 

መረጃ ማነፍነፊያ (ሰርች ኢንጂን) በኢንተርኔት አማካኝነት በአለማችን ከሚገኙ መካነ ድሮች ላይ መረጃዎችን በማነፍነፍ፣ በማደራጀት ለተጠቃሚዎች ተደራሽ ማድረግ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ነው፡፡ ይህ ቴክኖሎጂ ምጡቅ ቀመርን (አድቫንስድ አልጎሪዝም) የሚጠቀም ሲሆን ተፈላጊና መረጃዎችና የመረብ አድራሻዎችን በፈጣን ሰዓት ውስጥ ይጠቁማል፡፡ መረጃ ማነፍነፊያ በተለያየ መልኩ ጥቅም ላይ የሚውል ሲሆን ራሱን ችሎ እንደ ማነፍነፊያ መጠቀምና አንዳንድ መካነ- ድሮች ደግሞ የራሳቸው የሆነ አነስተኛና ብዙ አይነት የመረጃ ጥቆማ (ኢንዴክሲንግ) መንገዶች ያሉ ሲሆን በዋናነት ግን ቀጥለው የተዘረዘሩት ሶስቱ በስፋት ጥቅም ላይ ይውላሉ፡

 

1. መሉ ቃላትን መመዝገብ (Full-text indexing)

ይህ አይነቱ ዘዴ በድረ-ገፁ ላይ የሚገኙትን እያንዳንዱን ቃላት በመረጃ ቋት ውስጥ ይቀመጣሉ እነ ጎግል፣ አልታ ቪስታ እና ኢንፎ ሲክ ይህንን መንገድ ይጠቀማሉ

 

2. ዋና ዋና ቃላትን መመዝገብ (Key word indexing)

በድረ-ገፁ ላይ የሚገኙትን እያንዳንዱን ቃላት ከማስቀመጥ እንደላይከስ (Lycos)ያሉ በይነ መረብ መረጃ ማነፍነፊያዎች ዋና ዋና ወይም አስፈላጊ የሆኑትን ቃላት ብቻ ይመዘግባሉ።

3. በሰው በመታገዝ መመዝገብ (Human indexing)

ይህ አይነቱ መንገድ ሰዎች መረጃዎቹን ከድረ ገፆች ላይ በማየት የሚፈልጉት ቃላቶች ወይም ዐረፍተ ነገሮችን ብቻ በመምረጥ ወደ መረጃ ቋቱ እንዲመላከት ያደርጋሉ፡፡ ይህን መንገድ በብዛት የሚጠቀመው ያሁ የተሰኘው መረጃ አነፍናፊ ቴክኖሎጂ ነው፡፡ በውስጣች የሚገኘውን መረጃዎችን ብቻ የሚያፈላልጉበት ነው። ይህም የድረ-ገፁን ጎብኚዎች ቃላትን ወይንም ሀረግን ከድረ-ገፁ ፈልጎ ለማግኘት ይረዳል። መረጃ አነፍናፊዎች ስራቸውን እንዴት እንደሚከውኑና ከጀርባ ያሉትን ቴክኒኮች እንቃኛለን። የበይነ መረብ መረጃ አነፍናፊ ሦስት ዋና ዋና ደረጃዎች ያሉት ሲሆን እነዚህም ዌብ ክራውሊንግ፣ ዌብ ኢንዴክሲንግ እና ሰርቺንግ (መረጃ አሰሳ) የሰኛሉ፡፡

 

3. መረጃ አሰሳ (Searching)

 

ይሄኛው ክፍል ተጠዋሚዎችን ከዌብ ክራውለሩና ኢንዴክሰሩ ጋር በቀላሉ የሚያገናኝ ሲሆን ተጠቃሚዎችን ከመረጃ ማነፍነፊያ ቋት መረጃ የሚያገኙበት መስኮት ነው። ለምሳሌ ‘www.google.com’ ወይንም ‘www.yahoo.com’ በሚለው አድራሻ የምናገኘው ትእይንት(interface) ለመረጃ አሰሳ በብዛት ከምንጠቀምባቸው መንገዶች ዋነኞቹ ናቸው።

 

ኢትዮጲያ እንደ ጎግል አይነት መረጃ አነፍናፊ ቴክኖሎጂ ቢኖራት ሀገሪቱ እጅግ ብዙ ጥቅም ልታገኝበት ትችላለች። ለምሳሌ የተመረጡ ድረ-ገፆችን ኢንዴክስ በማድረግ አላስፈላጊ የመረጃ ክምችትን ማስወገድ እንችላለን ከዚህም ባሻገር ሃገራዊ በሆኑ ቋንቋዎች በርካታ ሰዎች መረጃዎችን ምግኘት ይችላሉ፣ ከገቢ አንፃር ስናየው ደግሞ ከማስታወቂያ እና ሌሎች መሰል ጉዳዮች ጥቅም በማስገኘት የገቢ ምንጭሊሆን ይችላል ። መረጣ ፖሊሲ በመጠቀም ተቋሞች በየስራ ዘርፎቻቸው የሚገኙና በይነ መረብ ላይ ያሉ ድረ-ገፆችን መዝግቦ መያዝና መጠቀም ይቻላል፡ ፡ ለምሳሌም አንድ በግብርና ላይ የሚሰራ ተቋም የራሱ የሆነ የመረጃ ማነፍነፊያ ቢኖረውና እሱን ተጠቅሞ በይነ መረብ ላይ የሚገኙ በግብርና ላይ የሚያትቱ ድረ-ገፆችን ብቻ ኢንዴክስ ቢያደርግ በግብርና ዙሪያ

የተጣራ መረጃን ለማግኘት ሌሎች መረጃ ማነፍነፊያዎች ከሚሰጡት ውጤት በተሻለና በተጣራ መልኩ መረጃውን እንዲያገኝ ያስችላል።

በማጠቃለያነትም ለጉዳዮ ትኩረት ተሰጥቶት በትምህርት ተቋማት፣ በአይቲ ዘርፍ በተሰማሩ ተቋማት ሰፊ ምርምር ተደርጎ ወደ ትግበራ ቢገባ የመረጃውን እጥረት ከመቅርፍ ባሻገር በልማቱም ጉልህ ሚና መጫወት ይቻላል፡፡

 

ምንጭ፡  ሳይንስ ቴክ ቅጽ 1፣ 2006

 

  

Related Topics