ሳምሰንግ ታጣፊ አንድሮይድ ስማርት ስልክ እየሰራ ነው ተባለ

 

ሳምሰንግ ታጣፊ አንድሮይድ ስማርት ስልክ እየሰራ ነው ተባለ

ሳምሰንግ ታጣፊ አንድሮይድ ስማርት ስልክ እየሰራ ነው ተባለ

 

 

 

 

 

የደቡብ ኮሪያው የቴክኖሎጂ ቁሶች አምራች ሳምሰንግ ታጣፊ ስልኮችን ዳግም ወደ ገበያው ለመመለስ እየሰራ መሆኑ ተሰምቷል።

ከዚህ ቀደም ስለ ታጣፊ ስልኮች ሲነሳ የሞቶሮላ ታጣፊ ስልክ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዝ ሲሆን፥ እንደ ኖኪያ እና ሳምሰንግ ያሉት ደግሞ ይከተላሉ።

ታዲያ አሁን ከሞባይል ገበያው የጠፋውን ታጣፊ ስልክ ሳምሰንግ በስማርት ስልክ መልክ ዳግም ሊመልስ መሆነ ነው ከኩባንያው አምልጠው የወጡ መረጃዎች የሚያመለክቱት። 

ሳምሰንግ አዲስ እየሰራ ነው የተባለው አዲሱ ታጣፊ አንድሮይድ ስማርት ስልክ “ጋላክሲ ፎልደር 2 / Galaxy Folder 2/” የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን፥ ኩዋል ኮም ፕሮሰሰር የሚጠቀም እና የባትሪ አቅሙ “2,000 mAh” ነው ተብሏል።

ታጣፊ አንድሮይድ ስማት ስልኩ 3.8 ኢንች ዲስፕሌይ ስክሪን፣ 8 ሜጋፒክስ የጀርባ ካሜራ እንዲሁም 5 ሜጋ ፒክስል የፊት ካሜራ የተገጠመለት ነው።

እንዲሆም 6.0.1 ማርሽማሎው አንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም የሚጠቀመው ስማርት ስልኩ፤ 2 ጊጋ ባይት ራም እና 8 ጊባ ባይት ሊሰፋ የሚችል የመረጃ መያዣ አለው።

የሳምሰንግ ታጣፊ አንድሮይድ ስማርት ስልክ መቼ ገበያ ላይ ይውላል በሚለው ዙሪያ የተባለ ነገር ባይኖርም፥ የመሸጫ ዋጋው ይሆናል ተብሎ የተቆረጠ ዋጋ ግን ተሰምቷል።

ይህም ስማርት ስልኩ ለገበያ ሲቀርብ አንዱ ስልክ እስከ 250 የአሜሪካ ዶላር ሊሸጥ ይችላል ተብሏል።

ምንጭ፦ www.techworm.net

 

  

Related Topics