Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

ወደ ስራ በመኪና የማደርገው ጉዞ አይፈጥንም ያለው ግለሰብ የግሉን አውሮፕ

 ወደ ስራ በመኪና የማደርገው ጉዞ አይፈጥንም ያለው ግለሰብ የግሉን አውሮፕላን ሰርቷል

 

ወደ ስራ በመኪና የማደርገው ጉዞ አይፈጥንም ያለው ግለሰብ የግሉን አውሮፕላን ሰርቷል

የ45 ዓመቱ የቼክ ሪፐብሊክ ዜጋ ፍራንቲሴክ ሀድራቫ ወደ ስራ በመኪና የማደርገው ጉዞ አይፈጥንም በማለት የግሉን አውሮፕላን ሰርቷል።

ግለሰቡ “ከቤቴ ወደ ስራ በተሽከርካሪ የማደርገው ጉዞ እስከ 14 ደቂቃዎችን ይወስድብኛል፤ ይህም በጣም ብዙ ነው” ያለ ሲሆን፥ አዲስ የሰራው አውሮፕላን ግን ጊዜውን በግማሽ ይቀንሳል ብሏል።

ሀድራቫ አውሮፕላኑን ከእንጨት የሰራ ሲሆን፥ ስራውን ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅም ሁለት ዓመት ፈጅቶባታል ነው የተባለው።

አውሮፕላኑ በሰዓት 146 ኪሎ ሜትር መብረር እንደሚችል ተነግሯል።

አውሮፕላኑን ሙሉ በሙሉ ገንብቶ ለመጨረስም 4 ሺህ 200 የአሜሪካ ዶላር ወጪ እንዳደረገበት ፍራንቲሴክ ሀድራቫ አስታውቋል።

በአሁኑ ጊዜም ግለሰቡ አውሮፕላኑን ተጠቅሞ ወደ ስራ መጓዝ ጀምሯል ነው የተባለው።

ሀድራቫ ከሚኖርበት አካባቢ ወደ ስራ ለመሄድ በፊት ከ12 እስከ 14 ደቂቃ እንደሚፈጅመበት የተናገረ ሲሆን፥ አሁን ላይ ግን ከ7 ደቂቃ ባነሰ ጊዜ ውስጥ እንደሚደርስ ተናግሯል።

ግለሰቡ ሁሌም አውሮፕላኑን ጠዋት 12 ሰዓት ላይ በማስነሳት ወደ ስራው ቦታ የሚበር ሲሆን፥ የሚሰራበት ፋብሪካ ፊትለፊት የሚገኝ ሜዳ ላይ ነው የሚያሳርፈው።

ከአውሮፕላኑ ከወረደ በኋላም በመግፋት ወደ ሚሰራበት ፋብሪካ በመውሰድ ቦታ እንደሚያስይዘው ተናግሯል።

ምንጭ፦ www.huffingtonpost.co.uk