የንቅሳት ቀለሞች ለካንሰር ያጋልጣሉ - ተመራማሪዎች

 

የንቅሳት ቀለሞች ለካንሰር ያጋልጣሉ - ተመራማሪዎች

የንቅሳት ቀለሞች ለካንሰር ያጋልጣሉ - ተመራማሪዎች

ነትን ለማስዋብ በማሰብ የሚደረግ የሰውነት ላይ ንቅሳት በርካታ ችግሮችን እንደሚያስከትል ተመራማሪዎች ይናገራሉ።

በተለይም ደግሞ ለንቅሳቱ ማድመቂያና ማሳመሪያ የሚሆኑት ቀለሞች ከቆዳ ላይ ጀምሮ ጠንከር ያለ የጤና እክል እንደሚያስከትሉም ነው የሚናገሩት።

ለአመታት የተደረጉ ጥናቶችን ተንተርሰው ባወጡት መረጃም፥ የንቅሳቱ ማዋሃጃ ቀለም የሚዘጋጅባቸው ውህዶች ለካንሰር ተጋላጭነት የሚዳርጉ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

እንደ እነርሱ ገለጻ ንቅሳቱን ማቅለሚያ የሚዘጋጁባቸው ውህዶች ካንሰር አምጭ እና አደገኛ ናቸው።

በአሜሪካ እና በአውሮፓ ታላላቅ የትምህርት እና የጤና ተቋማት የተደረጉ ምርምር እና ጥናቶች ለንቅሳት የሚውሉት ቀለሞች ካንሰር አምጭ መሆናቸውን ያሳያሉ ነው ያሉት።

እነዚህ ውህዶች ተዋህደው ቆዳ ላይ ካረፉ በኋላ በደም እና በኩላሊት በኩል ወደ ውስጥ ዘልቀው በመግባት የካንሰርን ህዋስ እንደሚያስፋፉም ነው የገለጹት።

ቀይ፣ ሰማያዊ እና አረንጓዴ ቀለሞች፦ በእነዚህ ቀለሞች ውስጥ የሚገኙ ውህዶች በውስጣቸው ከኒኬል እና ከብረት የሚገኘውን አንጸባራቂ ብረት (ኮልባት) እና ፈሳሹን ሜርኩሪ የያዙ ናቸው።

እነዚህ ውህዶች ደግሞ ካንሰር አምጭ ከመሆናቸውም በላይ ለቆዳ አደገኛ እና የማይመከሩም ናቸው።

ቀዩ ቀለም በውስጡ ሜርኩሪን ሲይዝ አረንጓዴ እና ሰማያዊ ደግሞ ኮልባትን ይዘዋል።

ሁለቱም በፊናቸው ሰውነት ላይ ጉዳት የማድረስ አቅም እና ካንሰርን የማምጣት እና ማስፋፋት እንሚችሉም ያስረዳሉ ተመራማሪዎች።

ጥቁር ቀለም፦ አውሮፓ ውስጥ ለዚህ ንቅሳት ማቅለሚያ ጥቅም ላይ ከሚውሉ 13 መቀመሚያዎች ውስጥ 13ቱ ካንሰር አምጭ እና አጋላጭ መሆናቸውን ተመራማሪዎቹ ገልጸዋል።

በአሜሪካ ደግሞ የካርበን እና ሃይድሮጅን ቅልቅል የሆነው ቤንዞፒረንን በመጠቀም ይሰራል።

ይህ ውህድ በእንስሳት ላይ ተሞክሮ የቆዳ ካንሰርን እንደሚያመጣም ባለሙያዎች ባደረግነው ጥናት አረጋግጠናል ብለዋል።

እናም ለንቅሳት ማድመቂያ ብለው የሚጠቀሟቸው ቀለሞች ከፍተኛ የሆነ የጤና እክልን እንደሚያስከትሉም ገልጸዋል።

እነዚህ ቀለሞች በተለይ ደግሞ ካንሰርን ያመጣሉና ቆም ብሎ ማሰቡ እንደሚበጅም ይመክራሉ።


ምንጭ፦ mycentralhealth.com

 

 

  

Related Topics