አዳም ስሚዝ -1- ስለ ቢዝነስ ሚስጥር አስፈላጊነት!

 

አዳም ስሚዝ -1- ስለ ቢዝነስ ሚስጥር አስፈላጊነት!

 

የadam smith ምስል ውጤት

አዳም ስሚዝ በቢዝነስ ውስጥ ሚስጥር አስፈላጊ እና ለተወሰነ ጊዜ ከፍ በሚል የገበያ ዋጋ ተጠቃሚ ሊያደርግዎት እንደሚችል ይናገራል። ይህ የአዳም ስሚዝ ትምህርት ዛሬም ድረስ አልተፋለሰም። Adam Smith goes on to say that if it ‘was commonly known their great profit would tempt so many new rivals to employ their stock in the same way, the effectual demand being fully supplied the market price would soon be reduced’. አዳም ስሚዝ ምን ማለቱ ይሆን?

ነገሩ ወዲህ ነው። የእርሶ ቢዝነስ በርካታ ተወዳዳሪ ስለሌለው ወይም የሆነ እርሶ ብቻ በሚያውቁት ሚስጥር ትርፋማ ከሆነ ያን ሚስጥርዎን መያዝ የቢዝነስዎ ህልውና ቁልፍ እንደሆን ያስተምርዎታል። ሚስጥርዎን ለሌላ ቢያካፍሉ ግን በገዛ እጅዎ ሌሎች ተወዳዳሪዎችን እንዲፎካከሩዎት ወይም የእርሶን ሚስጥር ተጠቅመው አመሳስለው እንዲሰሩ በሩን ከፈቱላቸው ማለት ነው። ይህ ደግሞ እርሶን መጀመሪያውኑ ከሌሎቹ ሰዎች የለየወት የያዟት ሚስጥር እንጅ ሌላ ስላልነበር በቢዝነሱ ላይ የርሶ ተጠቃሚነት አከተመ ማለት ነው። ምንም እንኳ ሚስጥርዎ ሁሌም ሳይደረስበት ሊቆይ ባይችልም እስከዚያ ድረስ ግን በሚስጥር ይያዙ!

ለዚህ ጥሩ ማሳያ ይሆነኝ ዘንድ ፋርማሲስቱን ዶ/ር ጆን ፔምበርተንን እኔ ላስተዋውቅዎ! ይህ ሰው እኤአ በ1886ዓ/ም በራሱ ቀመር ኮካ ኮላን የፈጠረ ነው። የኮካ ኮላን ሚስጥር ለማንም አልተናገረም። ምክንያቱም እሱን ከሌሎች የተለየ በገበያ ላይ ተጠቃሚ የሚያደርገው ያ ሚስጥር ብቻ ነው።ሌሎች ኮካ ኮላን ለመስራት ባደረጉት ጥረት ሌላ ብዙ መቶ አይነት የለስላሳ መጠጦች ተፈጥረዋል። ፔፕሲን ጨምሮ! በዚህ ሁሉ ሂደት ኮካ ኮላ ሚስጥሩን እንደያዘ ግን ውድድሩን በመፍራት ኮካ ኮላን ያሻሻለ መስሎት እኤአ በ1985ዓ/ም ‘ኒው ኮክ’ የሚል ምርት አቀረበ። ደምበኞቹ ሁሉ አዲሱን 'ኒው ኮክ’ አልወደዱትምና ግልብጥ ብለው ወደ ፔፕሲ ሄዱበት። የኮካ ኮላ ኩባንያ ወዲያኑ ኒው ኮክን ማምረት አቁሞ ቋጥሮ በያዛት ቀመር የሚሰራትን እና ዓለም የወደደለትን የምናውቀውን ኮካ ኮላ ወደ ማምረቱ ገባ። እነሆ እስከዛሬ ድረስ የዓለምን የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ ገበያ በበላይነት ይመራል።

አዳም ስሚዝ ይቀጥልና ‘Secrets in manufacturers are capable of being longer kept than secrets in trade.’ ይለናል። ይህ ከገንዘብ አቅም ጋር የተገናኘ ሳይሆን አይቀርም። የኔ ግምት ነው። ምክንያቱም ኢንዱስትሪዎችን እና አምራቾች ድርጅቶችን በቀላሉ መገንባት እና መወዳደር ከባድ በመሆኑ ነው። እዚህ ላይ በቅርቡ ቻይና የበርካታ የአሜሪካ ንግድ ተቋማትን ሚስጥራዊ ሰነዶች ድረገፃቸውን እና የመረጃ ቋታቸውን  ሰብራ(ሃክ አድርጋ) በርብራላች በሚል ከአሜሪካ ጋር ሲነታረኩ እንደነበር ልብ ይሏል። አንድ ላክልና ፅሁፌን ልቋጭ ‘A monopoly granted either to an individual or to a trading company has the same effect as a secret’.

እዚህ ጋር ግን ልብ በሉ። ለምሳሌ ወደ ኢትዮጵያ የሆነ ምርትን በብቸኝነት(በሞኖፖሊ) እንዲያስገባ መንግስት የፈቀደለት ሰው/ድርጂት ዘላቂ የሚሆነው ሌሎች ስላልተፎካከሩት ሳይሆን መንግስት ለሌሎቹ የሱ አይነት ስራ እንዲሰሩ ፍቃድ ስለማይሰጣቸው ወይም የሰውየውን ዓይነት ምርት በሃገር ቤትም እንዳይመረት የሚያደረግ አሰራር  በመተግበር ሰውየው/ድርጅቱ በብቸኝነት ህዝቡን እንዲያልብ ይፈቀድለታል ማለት ነው። ታዲያ ከዚህ ፍቃዱ ውጭ እንደ ኮካ ኮላ ወይም ሌላ የሆነ ነገር ፈጥሮ ወይም ላቡን አፍሶ ከሌሎች ጋር ፉክክር ውስት እገባለሁ ብሎ ስለማይጨነቅ ሁልጊዜም የምርቱ ጥራት አያስጨንቀውም። እንዲህ ያሉ አምራቾች/ድርጅቶች መንግስት በሞኖፖሊ የሰጣቸው ልዩ ፍቃድ ባበቃ በማግስቱ ከገበያ ይወጣሉ። ስለዚህ ለጊዜው ካልሆነ በቀር ሞኖፖሊ ጥሩ አይደለም። ገዥዎችም ጥራት በሌለው ምርት ውድ ዋጋ ከመክፈል እንዲድኑ እና ብዙ አማራጮችን አግኝኝተው በገበያ ላይ እንዲመርጡ ወዘተ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ሪፎርም ማድረግ ይገበዋል! ልብ በሉ! ኮካ ኮላን ለመፍጠር በሚል ብዙዎች ወደ ሙከራ እና ፈጠራ ገብተው ብዙ ለስላሳ መጠጦችን መፍጠር የቻሉት ነፃ የገበያ ውድድር በመኖሩ ነበር።ያ ደግሞ ለኢኮኖሚው አጋዥ የሆኑ በርካታ ፋብሪካዎች እንዲቋቋሙ በዚያም ብዙዎች የስራ እድል እንዲፈጠርላቸው ምክንያት ሆኗል።  ኮካኮላ በሞኖፖሊ ከአሜሪካ መንግስት ጋር በሽርክና ወይም በልዩ ፈቃድ የሚሰራበት መንገድ ቢኖር ግን መጀመሪያውኑ እነዚያ ብዙ መቶ የለስላሳ አይነቶችን የፈጠሩት ሰዎች ተነሳሽነቱ አይኖራቸውም ነበር። የሰዎች የግል ተነሳሽነት ከሌለ ደግሞ ሰዎችን የቱንም  ያህል እያደራጀህ ብር ብትደጉማቸው የሃገር ሃብት ከማባከን በቀር ምንም ፋይዳ የለውም።

ምንጭ፡-Personal Librere