አሰር ስክሪኑ የሚታጠፍ ላፕቶፕን አስተዋውቋል

 

አሰር ስክሪኑ የሚታጠፍ ላፕቶፕን አስተዋውቋል

 

ግዙፉ የታይዋን ኮምፒውተር አምራች ኩባንያ አሰር በአይነቱ ለየት ያለ ላፕቶፕን አስተዋውቋል።

ኩባንያው በበርሊን በተካሄደ የዘርፉ ኮንፈረንስ ላይ ስክሪኑ የሚታጠፍ ላፕቶፕ መስራቱን ይፋ አድርጓል።

“21 ኤክስ” የሚል መጠሪያ የተሰጠው ይህ ላፕቶፕ 21 ኢንች የስክሪን ስፋት ያለው ነው ተብሏል።

በቴሌቪዥን እና በተንቀሳቃሽ ስልኮች የተጀመረው ተጣጣፊ ቴክኖሎጅ አሁን ደግሞ ወደ ላፕቶፑ ዞሯል።

በዘርፉ የመጀመሪያ የሆነው ላፕቶፕ እጅግ ዘመናዊ መሆኑንም ኩባንያው ገልጿል።

1080 ግራፊክ ካርድ ያለው ላፕቶፕ እጅግ ጥርት ያለ ምስልን ለማየት እንደሚያስችልም ነው ኩባንያው የገለጸው።

ላፕቶፑ በስራ ላይ እያለ ምናልባት ሙቀት ቢያጋጥመው እንኳን 5 ማቀዝቀዣዎች እንዳሉት ተገልጿል።

እስከ 64 ጊጋ ባይት ውስጣዊ የመያዝ አቅም ያላቸው አራት ራሞች ሲኖሩት፥ አራት ቴራ ባየት መጠን ያላቸውን መረጃዎች ደግሞ ከፍላሽ እና መሰል ነገሮች መቀበል እና መያዝ ይችላል።

ከፍተኛ አቅም ያለው እና ከእስካሁኖቹ የላፕቶፕ ከፍ ያለ ፕሮሰሰር እንዳለውም የኩባንያው መግለጫ ያስረዳል።

ታዲያ ይህን ዘመናዊና ለየት ያለ ላፕቶፕ የግሉ ማድረግ የፈለገ 5 ሺህ የአሜሪካ ዶላር መክፈል ግድ ይለዋል።

በፈረንጆቹ 2017 የመጀመሪያ ወራት ደግሞ ገበያውን እንደሚቀላቀል ይጠበቃል።

 

 

 

ምንጭ፦ fossbytes.com/

 

  

Related Topics