ስሱ ቆዳን መንከባከብ

 

Beauty Tips


የቆዳ ድርቀት የሚከሰተው ሰውነት በቆዳ ላይ እንደማገጃ የሚያገለግል በቂ ቅባት ባለማመንቸቱ ምክንያት የቆዳ ድርቀትና ቆዳ መቆጣትን አስከትሎ ቆዳ ለመነፋፋት የተጋለጠ እንዲሆን ሲያደርገው ነው፡፡ ቆዳ ድርቀት ፊት፣ እጅ፣ እግር፣ ተረከዝና ሆድን ጨምሮ በሁሉም የሰውነት ክፍሎች ላይ ሊከሰት ይችላል፡፡

ስሱ ቆዳን እንዴት መለየት ይቻላል?
ስሱ የሆነ ቆዳ ሽፍታ ያለበትና ሲነኩት ሕመም የሚሰማበት ነው፡፡ በጣም በፍጥነት ሊቆጣ የሚችል ሲሆን ለያክኩት የሚያምም እከክ ሊፈጥር ይችላል፡፡ ቆዳው በአጠቃላይ ደረቅ፣ የሚቀረፍና ምቹነት የሌለው ነው፡፡ ቀጥታ የፀሐይ ብርሃንና ሙቀት ቆዳ እንዲፈነዳና እንዲቆጣ ያደርገዋል፡፡

የስሱ ቆዳ መንስኤዎች


የአለርጂክ ምላሾች፣ የሆርሞን መጠን መዛባት፣ ጭንቀትና ዘረ መል ጉዳዮች በሙሉ በቆዳ ስሱነት ላይ የበኩላቸውን ድርሻ ይወጣሉ፡፡ ማንኛውም የቆዳ ዓይነት በአንድ ወቅት ወይም በሌላ ጊዜ ስሱነት ሊያጋጥመው እንደሚችል ማስተዋል ያስፈልጋል፡፡ የአመጋገብ ሁኔታም ስሱነት ላይ ተጽእኖ የሚያሳድር ሌላ ጉዳይ ነው፤ የአልሚ ምግብ እጥረትና በቂ ያልሆነ የፈሳሽ አቅርቦትም ዋነኛ አስተዋጽኦ አድራጊዎች ናቸው፡፡ ስሱ ቆዳ ያላቸው ሰዎች በየቀኑ ኦሜጋ 3 ፋቲ አሲዶችን እንዲወስዱ የሚመከር ሲሆን ይህ አሲድ ቆዳን የሚያጠነክርና ተጨማሪ እርጥበትን የሚሰጥ ነው፡፡ እንደ ትልቅ ዓሣ ያሉ ምግቦችና ሌሎች ዘይታማ የዓሣ ዓይነቶች፣ ጠንካራ ሽፋን ያለው ፍራፍሬና የተልባ ፍሬ በሙሉ ከፍተኛ መጠን ያለው ኦሜጋ 3 ፋቲ አሲዶችን በውስጣቸው ይይዛሉ፡፡
መዓዛማ፣ ቀለም አመንጪና የተወሰኑ ኬሚካሎችና ማድረቂያዎች ቆዳን የመጉዳት ባህርይ ስላላቸውና ስሱ እንዲሆን ስለሚያደርጉት ከእነርሱ መራቅ ያስፈልጋል፡፡ ተለዋዋጭ የሙቀት መጠንና የእርጥበት መጠን የመሳሳሉ ወቅታዊ ለውጦችም ለቆዳ ስሱነት አስተዋጽኦ ያደርጋሉ፡፡

 

የቆዳ ስሱነት ችግር ያለባቸው ሰዎች የሚከተሉትን ነገሮች ማራቅ አለባቸው፡
• ጠንካራ ማጽጃዎች፣ ሳሙናዎች፣ ከፍተኛ አረፋ የሚያመነጩ የሰውነት ማጠቢያዎችና ሻምፑዎች፡፡
• መዓዛ ያላቸው ምርቶች፡፡
• ብሩህ ቀለም ያላቸው የገላ መታጠቢያና የሰውነት መጠቀሚያ ምርቶች፡፡
• ቆዳን ሊጭሩና ሊያስቆጡ የሚችሉ እንደ ሱፍና የፍየል ጸጉር የመሳሰሉ ጨርቆችን፡፡
• ቆዳ እንዲቀላ ሊያደርጉ የሚችሉ ትኩስና ቅመም የበዛባቸው ምግቦች፡፡
• ቆዳ ፈሳሽ እንዲወጣ የሚያደርጉ አልኮልና ቡና፡፡
•በቀጥታ ለፀሐይ ብርሃን የሚያጋልጥ ሁኔታ፡፡

እንደ መልካም ዕድል ሆኖ፣ ስሱ ቆዳን በተለይ ለመንከባከብ ተብለው የተዘጋጁ በርካታ የቆዳ እንክብካቤ ምርቶች አሉ፡፡ እነዚህ ምርቶችም ቆዳን ለማለስለስ፣ ለማገገምና የመከላከል አቅሙን ለመገንባት ያግዛሉ፡፡
Vaseline dry skin repair lotion ስሱ የሆነ ቆዳ ላለባቸው ሰዎች በጣም ተመራጭ የሆነ ማለስለሻ ነው፡፡ Vaseline dry skin repair ሎሽን በተለይ የተዘጋጁ የግላይሰሪን (እርጥበትን በሁሉም የቆዳ ሽፋኖች ለማዳረስ) እና የ Vaseline® Petroleum Jelly ጥቃቅን ጠብታዎች (እርጥበቱን ይዞ ለማስቀረት) ውህዶችን የያዘ ነው፡፡ ደረቅ ቆዳን ለ3ጊዜና ከዚያ በላይ ማገገም እንደሚችል በሕክምና ምርመራ የተረጋገጠለት ነው፡፡

ምንጭ፥Look Good Center