ሻምበል አበበ ቢቂላ አጭር የህይወት ታሪክ

 

ሻምበል አበበ ቢቂላ (Abebe Bikila)

 

 

ሻምበል አበበ ቢቂላ በደብርሃን ከተማ በደነባ ልዩ ስሟ ጃቶ የምትባል ቦታ ከአባቱ አቶ ቢቂላ ደምሴ እን ከእናቱ ወ/ሮ ውድነሽ መንበሩ ነሐሴ 30 ቀን 1925 ዓ.ም. ተወለደ:: አበበ የቄስ ትምህርት እንደተማረና ከልጅነቱ ጀምሮ የገና ጨዋታ ጎበዝ እንደነበረ ይነገራል:: በመሆኑም ወደ አዲስ አበባ በመሄድ በክብር ዘበኛ በወታደርነት ተቀጠረ::

የ1948ቱ የሜልቦርን ኦሎምፒክ ኢትዮጵያን ወክለው የተሳተፉት አትሌቶች የለበሱት ዩኒፎርም እና አገራቸውን ወክለው መሮጣቸው የፈጠረበት መነሳሳት በሀገር ውስጥ የሚደረጉ የ5ሺ እና 10ሺ ሜትር ውድድሮች ላይ መካፈል ጀመረ:: በወቅቱ በጀግናው ዋሚ ቢራቱ ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን በማሻሻል እውቅናን አገኘ:

 

ለ1952 ዓም የሮም ኦሎምፒክ እንዲሳተፍ ከሲውድናዊ አሰልጣኙ ኦኒ ኒስካነን ጋር በጫማም በባዶ እብሩም መለመዳዱን እና በጊዜው በጫማ በሚለማመድበት ሰዓት የተወሰነ ይዘገይ እንደነበረ ይነገራል:: በመሆኑም በባዶ እግሩ ተወዳድሮ ክብረ ወሰን በማሻሻል እና በማሸነፍ የመጀመሪያው  የጥቁር ታላቅ አትሌት ሆነ::  በዚህም ድል የተነሳ የጣልያን ጋዜጠኞች“ኢትዮጵያን ለመውረር የጣልይን አገር ወታደር ሁሉ አስፈልጎ ነበር ኢትዮጵያ ግን አንድ ወታደር ብቻ ልካ ድፍን ሮምንወረረችው” ሲሉም ዘግበው ነበር:: በዚህም የተነሳ Bikila የሚል ከጋዶ እግር ጋር የሚመሳሰል ጫማ ተሰርቶ በአገልግሎት ላይ ይገኛል::

 

ከዚህ ድል መልስ የከሸፈው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ጋር በተያያዘ አበበ ተጠርጥሮ ለተወሰነ ግዜ ታስሮም ነገር:: ሁለተኛ የኦሎምፒክ ወርቁንም 1957 ዓ.ም. በቶክዮ አሸንፉአል:: ከዚህም በተጨማሪ በብዙ የአለማቀፍ የማራቶን ውድድር በአንደኛነት ማጠናቀቁ ይገለጻል::  

 

አበበ ከወ/ሮ የውብዳር ወ/ጊዮርጊስ ጋር በትዳር 4 ልጆችን ያፈሩ ሲሆን 1961 ዓ.ም. በተሽለማት መኪና በመንቀሳወስ ላይ እንዳለ አደጋ ደርሶበት ለ5 ዓመታት ከወገቡ በታች ሽባ ሆኖ 1966 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም ተለይቷል::

ምንጭ፡-ሰዋሰዉ