ጢሥ አባይ ፏፏቴ

 በጢስ አባይ ከተማ ወይም ከባህር ዳር በስተምስራቅ  30 ኪሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ፏፏቴ ነው። ፏፏቴው የሚፈጠረው የአባይ ወንዝ ትልቀቱ

በግምት ከ40 እስከ 50 ሜትር እና ስፋቱ 400 ሜትር የሚሆን ገደል ውስጥ ተውርውሮ ሲገባ ነው።

 የአባይ ውሃ ወደዚህ ገደል ሲወረወር እጂግ ማራኪ የሆነ የነጎድጏድ ድምፅ እና አካባቢውን እንደ ጢስ የሚሸፍን የውሃ ብናኝ ይስተዋላል።

 በተወሰነ ጊዜ ልዩነትም ብልጭ እያለ የሚጠፋ ቀስተ ደመና ይታያል።

 

 
 
                
 

ከባህር ዳር ከተማ ተነስቶ ወደ ጢሥ አባይ ከተማ የሚሄድ የመኪና መንገድ ያለ ሲሆን፤ ከከተማዋ አንስቶ ደግሞ ወደ ፏፏቴው ለመሄድ ሁለት   አማራጮችን መጠቀም ይቻላል።  አንደኛው  አማራጭ  ከከተማዋ 1.5 ኪሜ ያክል በመኪና ከተጏዙ በሇላ ቁልቅለት እና አቀበት የሆነውን

የእግር መንገድ ለ20 ደቂቃ ተጉዘው ፏፏቴው ጋር መድረስ ይቻላል። በዚህ መንገ ሲሄዱ እግረመንገድን በ17ኛው ክፍለ ዘመን 

በአፄ ሱስንዮስ ዘመነ መንግስት እንደተሰራ የሚነገርለት የአላታ ድልድይን ማየት ይቻላል።

 
 
                
 

ሁለተኛው አማራጭ ደግሞ እዚያው ወንዙ አጋባቢ በሚሰራ "ደንገል" በመባል የሚታወቅ ጀልባ በመጠቀም እዚያው ፏፏቴው ድረስ መሄ ይቻላል።

በዚህም አማራጭ ፏፏቴው ለመድረስ በአጠቃላይ ከ30 እስከ 40 ደቂቃ ይወስዳል።

 

ምንጭ

      - የአማራ ክልል የቱሪሥት መሥህብ ሃብቶች (የአማራ ቱሪዝም እና ማሥታወቂያ ቢሮ)