Tenders

 

Type: Construction

 

Organization: የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚ/ር

Dead Line: 2016-01-28

 

Tender Detail:

 

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚ/ር (የፒሲቢ (PCB-print circuit board) ላቦራቶሪ የተለያዩ ማሽኖችና ተያያዥ ዕቃዎች)  ግዢ በሃገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች /ተወዳዳሪዎች/ተጫራቾች፡-

  1. በመስኩ ተዛማጅነት ያለው የታደሰ የንግድ ፍቃድ ኮፒ
  2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የሚገልፅ ሰርተፊኬት ኮፒ
  3. ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለሥልጣን የተሰጠ ማስረጃ ኮፒ
  4. ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡመሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል
  5. ተወዳዳሪዎች ከታወቀ የpcb ማሽን አምራች ኩባንያ ፍቃድ የተሰጣቸው ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል
  6. የጨረታ ማስከበሪያ ብር የጠቅላላ ዋጋውን 1% ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው
  7. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በቅሎ ቤት በሚገኘው የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ አጠገብ የሚኒስቴር መ/ቤቱ የንብረት አገልግሎት አቅርቦት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 08 በመቅረብ መግዛት ትችላላችሁ
  8. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በሁለት ኤንቨሎፕ የቴክኒክና ፋይናንስ ዋናና ኮፒ በማለት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ በሚውልበት የመጨረሻው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ጨረታውም በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 3፡30 የጨረታ ሳጥን ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የንብረት አገልግሎት አቅርቦት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 08 ይከፈታል
  9. የጨረታው አሸናፊ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና 10% /አሥር በመቶ/ (CPO) በማስያዝ ከመ/ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማል

ተጫራቾች ማንኛውም የመንግስት ታክስና ግብር ግዴታቸውን በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ነጠላ ዋጋ ውስጥ አካተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል

መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስልክ ቁጥር 011 896 17 02

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስተር