Tenders

 

Type: Building Materials

 

Organization: ፋይናንስና ሀብት አስተዳደር ዲቪዥን ሉሲ ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት

Dead Line: 2016-02-24

 

Tender Detail:

 

የሚሸጥ ይዞታ ይፈለጋል

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

አክሲዮን ማኅበራችን ዋስትና ገብቶላቸው ጉዳት የደረሰባቸውን የደንበኞቸ ንብረቶች የሚያቆይበት ንብረት የሰፈረበት ክፍት ማቆያ ቦታ (open yard) የጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈረቶች የሚያሟሉና በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የቦታ ይዞታ ያላቸውና በስማቸው የተያዘ ቦታ በሽያጭ ለማስተላለፍ ፍላጎት ያላቸው በጨረታው ሊወዳደሩ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  1. የይዞታ ማረጋገጫ ሰርተሪኬተ /ካርታ ያላቸው
  2. በቦታው ላይ የሰፈረ ቤት /ቋሚ ንበረት/ ለምሳሌ መኖሪያ ቤት፣ መጋዘን፣ በረት የመሳሰሉ
  3. የቦታው ስፋት ከ3000 እስከ 5000 ስኩዌር ሜትር የሆነ
  4. ዕዳ፣ ዕገዳና የይገባኛል ክርክር የሌለበት
  5. ከባድ ተሽከረካሪ መኪኖችን ማስገባት ከሚያስችል መንገድ ጋር የተገናኘ

ከዚህ በላይ የተገለጹትን መስፈርቶች አሟልተው መሸጥ የሚፈልጉ ባለይዞታዎች/በሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ውክልና ያላቸው ሕጋዊ ሰነዶችን ጭምር በማያያዝ የሚሸጡበትን ዋጋ በስም በታሸገ ኢንቬሎፕ በማድረግ የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን እስከ የካቲት 16 ቀን 2008 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ በሚከተለው አድራሻ እንዲያቀርቡ ተጋብዘዋል፡፡

ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ሰነዱ የካቲት 17 ቀን 2008 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 በዋናው መ/ቤት 7ኛ ፎቅ በቦርድ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ አክሲዮን ማኅበራችን በጨረታው ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የማይገደድ መሆኑን በቅድሚያ እናስታውቃለን፡፡

አድራሻ፡- ፋይናንስና ሀብት አስተዳደር ዲቪዥን

ሉሲ ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት

አዲስ አበባ

ቢሮአችን የሚገኘው በቴሌ ጋራዥና በጠመንጃ ያዥ የንግድ ባንክ ቅርንጫፍ መካከል ባለው ሙጅብ ታወር 7ኛ ፎቅ

ማብራሪያ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር 0114-703361/0912 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡