Tenders

 

Type: Construction

 

Organization: አድስ አበባ ከተማ

Dead Line: 2016-01-28

 

Tender Detail:

 

በአድስ አበባ ከተማ አስተዳደር የውበት፤መናፈሻ ዘላቂ ማረፊያ ልማት አስተዳደር ኤጀንሲ በልደታ ክፍለ ከተማ የመዋኛ ገንዳ ተዛማች የግንባታ ስራቾች ወይም (LIDETA SWIMMING POOL INTEGRATED ACCESSORY CONSTRUCTION WORKS OF BLOCKS 1$2 GUARD HORSE FENCE AND ELECTRICAL AND SANITARY INSTALLATIONS) በደረጃ 5 እና ከዚህ በላይ ሥራ ተቋራጮችን በተጠየቀው ደራጃ በቂ ልምድና ሙያ ያላቸውና የሥራ ተቋራጮች በጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡ስለዚህም በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ የሥራ ተቋራጮች የሚከተሉት ማሟላት አለባቸው፡፡

  1. በዘርፉ ለ2007/08 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረባ የሚችል፡፡

  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ

  3. የዘመኑ ግብር የከፈለ

  4. ለ2008 ዓ.ም የታደሰ የሥራና ከተማ ልመት ሚኔስቴር የባለሙያዎች ምስክርነት ወረቀት (professional license እና ከዚህ በላይ)ማቅረብ የሚችል፡፡

  5. የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል መሆን አለባቸው፡፡

  6. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት 15 የሥራ ቀናት ውስጥ ሰነዱን በአዲስ አበባ አስተዳደረ የውበት፤መናፈሻ ዘላቂ ማረፊያ ልማት እና አስተዳደር ኤጀንሲ  መግዛት ይችላሉ፡፡

  7. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ሰነድ ፋይናንሺያል እና ቴክኒካል ለእያንዳዱ ዋጋውንና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻ የፕሮጀክቱ ስምና አድራሻ በመጥቀስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እስከ 16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ሥራ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨራታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

  8. ተጫራቾች የጨረታው ማስከበሪያ(bid bond)ያስገቡትን ዋጋ ብር 50,000 ብር(ሀምሳ ሺህ ብር ብቻ)በባንክ በተረጋገጠ ቼክ(cpo)ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በ16ኛው የሥራ ቀን 2008 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የውበት መናፈሻና ዘላቂ ማረፊያ ልማት አስተዳደር ኤጀንሲ ይከፈታል፡፡የመክፈቻውም ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡

  9. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011558 11 79 ደውለው ይጠይቁ፡፡

  10. ኢጀንሲው ጨረታውን በሙሉ ሆነም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡