Tenders

 

Type: Autos

 

Organization: የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማህበር

Dead Line: 2016-02-26

 

Tender Detail:

 

የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማህበር

የሞተር ሳይክሎችን ለመግዛት በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማህበር በበጎ ፈቃደኞች ተሳትፎ ላይ የተመሰረተ ለትርፍ ያልተቋቋመ አገር በቀል መንግስዊ ያልሆነ ድርጅት ነው፡፡ የተቋቋመበት ተልእኮም ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በተለይም የእናቶችንና ህፃናትን ጤንነትን ለመጠበቅ እንዲሁም ሴቶችና ወጣቶች ጥራቱን የጠበቀ እና ሁሉን አቀፍ የሆነ አማራጭ የስነ-ተዋልዶ ጤና አገልግሎት እንዲያገኙ ማስቻል ነው፡፡

የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማህበር ለማህበረሰቡ የሚሰጠውን አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ እንዲችል በሱማሌ ክልል እና በደቡብ ክልል በሚገኙ የአርብቶ አደሩ አካባቢዎች ለሚተገብረው የ RIF ፕሮጀክቶች ማስፈፀሚያ የሚያገለግሉና ከዚህ በታች በሰንጠረዥ ውስጥ የተዘረዘሩትን መስፈርች (እስፔሲፊኬሽንስ) በሚያሟላ መልኩ የሞተር ሳይክሎችን ማቅረብ የሚችሉ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ 

ተ.ቁ

ብዛት

መግለጫ

2

25

-          Motorcycle 150cc and above

-          Ground clearance 250mm & above; Fuel tank capacity 7L & above

-          Convenient for off-road transport service (Rural & Desert Area)

በመሆኑም

  1. የ2008ን የመንግስ ግብር የገበረ እና በዘርፉ ላይ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው፣
  2. የጨረቃ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ /የጨረታ ዋጋውን 1% በሲፒኦ ወይም በባንክ /ኢንሹራንስ ዋስትና ማቅረብ የሚችል፤
  3. እቃዎቹን ውል በተፈረመና በውል በተጠቀሰ በአስራ አምስት ተከታታ ቀናት ጊዜ ውስጥ ማቅረብ የሚችል፣
  4. ተጫራቾች የሞተር ሳይክሎቹን የሚያቀርቡበትን ዋጋ፤ የድርጅታቸውን ህጋዊ ሰነዶችንና፣ ዝርዝር አስፔሲፊኬሽን፤ የሚያሳይ ማንዋልና ፎቶዎች፤ እንዲሁም ሌሎች አጋዥ ዶክመንቶችን ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ የአማርኛው እትም ከወጣበት ቀን አንስ እስከ 10ኛው ቀን ማለትም እስከ አርብ የካቲት 18 ቀን 2008 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በስም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማህበሩ ዋና መ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በጨረታ መክፈቻ ላይ መገኘት በሚፈልጉ ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእለቱ አርብ የካቲት 18 ቀን 2008 ዓ.ም በ8፡00 ሰዓት በዋናው መ/ቤተ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  5. ማህበሩ ጨረታው በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ ወይም የሚገዛውን መጠን የመቀየር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማህበረ ዋናው መ/ቤት ደበረዘይት መንገድ፣ መስከረም ማዞሪያ ሪቼ አካባቢ (በቅሎ ቤት)

ስልክ ፡  251 114 67 23 00                     Fax:    251 114 67 10 84