Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: የከሰረው ሆላንድ ካር ኃ.የተ.የግል ማህበር

Dead Line: 2016-02-27

 

Tender Detail:

 

የከሰረው ሆላንድ ካር ኃ.የተ.የግል ማህበር ሞጆ የሚገኘውን የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ፣ የተገጣጠሙና ያልተገጣጠሙ መኪናዎች፣ በፋበሪካውና መጋዘን ውስጥ ያሉትን ነብረቶች፣ ማሽኖች፣ መለዋወጫ ዕቃዎችን የንብረት ቆጠራ እና የማስታረቅ ስራ ለማሰራትና በልዩነት (በጉድለት) የታወቁ ንብረቶችን ለመለየት ስቶክ ኦዲት ማድረግ የሚችሉ ባለሙያቆችን ወይም ድርጅቶችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ሙያው፣ የስራ ፈቃዱና ልምዱ ያላችሁ ባለሙያዎች ወይም ድረጅቶች ማስረጃችሁን በመያዝ ከመጋቢት 8 ቀን 2008 ዓ.ም እስከ መጋቢት 10 ቀን 2008  ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 -11፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ሞጆ ከተማ በሚገኘው ሆላንድ ካር የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ ገቢ በመገኘት ንብረቶቹን ባለበት ቦታ አንድትመለከቱ ሆኖ በመቀጠልም የንብረት ቆጠራ ለማድረግ፣ ለማስታረቅና የጎደሉ (በልዩነት የታዩ) ንብረቶችን ለመስራት የመስሪያ ዋጋችሁን ከመጋቢት 12 ቀን 2008 ዓ.ም እስከ መጋቢት 20 ቀን 2008 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 10፡30 ሰዓት ድረስ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማህበሩ ጽ/ቤት ራስ ሆቴል 2ኛ ፎቅ እንድታቀርቡ እየጋበዝን፣ የጨረታው ሰነድ መጋቢት 24 ቀን 2008  ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት በማህበሩ ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት መሆኑን ያስታውቃል፡፡

ማህበሩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0921383837/0911125677 መጠየቅ ይቻላል፡፡

የከሰረው ሆላንደ ካር ኃ.የተ.የግ ማህበር ጽ/ቤት