Tenders

 

Type: Accounting / Audit

 

Organization: ሕዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር

Dead Line: 2016-04-13

 

Tender Detail:

 




  1. ሕዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር የ2008 በጀት ዓመት የሒሳብ ምርመራ የሚያከናውን የውጭ ኦዲተር በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

የጨረታ ማወዳደሪያ መስፈርት

ሀ) ሒሳብ ለመመርመር የሚያስችል ህጋዊ ፈቃድ ከፌደራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ወይም ከአ/አ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መ/ቤት የተሰጠው እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆነ፣

ለ) የዘመኑን ግብር ከፍሎ የሙያ ፈቃዱን ያሳደሰ፣

ሐ) የግብር መለያ ቁጥር /ቲን/ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፣

መ) በሒሳብ ምርመራ ስራ ላይ በቂ ልምድ ያለው፣

ሠ) ከዚህ ቀደም የመረመራቸውን ድርጅቶች የስራ ልምድ ማቅረብ የሚችል፣

ረ) በሙያው ላበረከተው በጎ ተግባር በኦዲት ተደራጊዎችና በሌሎችም ሶስተኛ ወገኖች /አበዳሪዎች/ የተሰጠ የምስጋና ወረቀት ካለ ማቅረብ የሚችል፣

ሰ) ለአገልግሎት ክፍያ የሚያስፈልገውን የገንዘብ መጠን ታክስን ጨምሮ ስራውን አጠናቆ ለማስረከብ የሚፈጀውን ጊዜ በመጥቀስ ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርበታል፡፡

  1.  ተጫራቾች የሚያቀርቡት
  • አንድ ዋና () የጨረታ ሰነድ ለብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ ታሽጎ
  • አንድ ቅጂ () የጨረታ ሰነድ ለየብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ ታሽጎ እንዲሁም፣
  • ሁሉም በአንደ ላይ በትልቅ በሰም በታሸገ ፖስታ ውስጠ ተካቶ የታሸገ መሆን አለበት፡፡
  • በዋናውና በቅጂው መካከል ልዩነት ቢፈጠር ዋናው ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡ የተሰረዘ ሰነድ በፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡
  1. ተጫራቾች ያለአገልግሎት ስራውን የሚሰሩበትን የጠቅላላ ዋጋ 2  (ሁለት በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የባንክ ክፍያ ማዘዣ () ለህዳሴ ቴሌኮም አ.ማ በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ ሚያዝያ 4 ቀን 2008 ዓ.ም እስከ ከቀኑ 10፡30 ድረስ ‹‹ህዳሴ ቴሌኮም አ.ማ›› ደብረዘይት መንገድ ጠመንጃ ያዥ ባንክ ፊት ለፊት የሚገኘው ቤተሳይዳ ሕንጻ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ፕሮኪዩርመንት ዋና ክፍል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን ማስገባት የሚችሉ ሲሆን፣ ጨረታውን የመክፈቻ ቀን ሚያዝያ 5 ቀን 2008 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሙጂብ ታወር 8ኛ ፎቅ የጨረታው የሚከፈት ይሆናል፡፡
  3. ከላይ የተገለጸውን መመሪያ ባልተከተሉ ተጫራቾች ላይ ወዲያውኑ ጨረታው የሚሰረዝ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  4. ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0118 – 968332 ፋክስ ቁጥር 0114 663649 መጠቀም ይችላሉ፡፡
  5. ህዳሴ ቴሌኮም አ.ማ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ሕዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር