Catagory Lists
Tenders
Type: Construction
Organization: ሲዳማ ዞን የጎርቼ ወረዳ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ጽ/ቤት
Dead Line: 2016-04-06
Tender Detail:
የሲዳማ ዞን የጎርቼ ወረዳ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ጽ/ቤት በጎርቼ ወረዳ ውስጥ በሀይሰዊጣ ቀበሌ ውስጥ የውሀ ቦኖን ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት፡-
- ደረጃቸው 9 እና ከዚያ በላይ ሆነው በውሃ እና ተዛማጅ ዘርፍ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው፣
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የ2008 ዓ.ም ግብር የከፈለበትን መረጃ ማቅረብ የሚችል፣
- በግንባታ ሂደት ችግር ምክንያት ማስጠንቀቂያ ያልተሰጠውና የጥሩ አፈፃፀም ሰርተፊኬት ያለው፣
- የጨረታው ማስከበሪያ () ከሚያቀርበው የጠቅላላ ዋጋ 1 በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ () የየባንክ ጋራንት ማስያዝ የሚችል፣
- ተጫራቾች የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ7 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ 150.00 /አንድ መቶ ሀምሳ ብር/ በጎርቼ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ከፍለው ገንዘቡ የተከፈለበትን ደረሰኝ በማቅረብ ከጎርዤ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት መ/ፋ/አስ/ስራ ሂደት የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፣
- ለጨረታው ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሰረት ተሞልቶ ኦርጅናልና 2 ፎቶ ኮፒዎች ለየብቻቸው በሰም ታሽጎ ሁሉም ዶክመንት በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት የማስታወቂያ ከወጣበት በ8ኛ የስራ ቀን ከጠዋቱ 5፡00 እስከ 6፡30 ሰዓት በጎርቼ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት /ባልተገኙበት/ ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይከፈታል፣
- የወቅቱን የገበያ ዋጋ ያላገናዘበ ጨረታ ተቀባይነት አይኖረውም ከቀረበው የዋጋ ትንታኔ መያያዝ አለበት፣
- አሸናፊው ተጫራች ከባንክ /ከአደራጁ መ/ቤት ከኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል፣
- አሰሪው መ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በስራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡
በሲዳማ ዞን የጎርቼ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት