Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: ጊዶሌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

Dead Line: 2016-04-05

 

Tender Detail:

 



ንብረትነቱ የጊዶሌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
የሆነና በአንድ ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ፣ ከጊዶሌ ከፍተኛ 2ኛ ደ/ት/ቤት መሰናዶ ት/ቤት አጠገብ /በላይ/ ያለ ባህር ዛፍ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚሀ መወዳደር የምትፈልጉና ከዚህ በታች መስፈርቶችን የምታሟሉ ነጋዴዎች እንድትወዳደሩ እናሳውቃለን፡፡

ለመወዳደር የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች፡-

  • የዘመኑ ግብር የከፈለና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፣
  • የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin No) ያለው፣
  • በዘርፉ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያለው እና የደን ውጤቶች የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ከሆነ መረጃ ማቅረብ የሚችል፣
  • በሌሎች የማጭበርበር ስራዎች ያልቴዘ፣
  • ከሌሎች ተጫራቾች በጠቅላላ ዋጋ ድምር ከፍተኛ ዋጋ ማቅረብ የሚችል፣
  • አሸናፊው ድርጅት ባሸነፈ 15 ቀናት ውስጥ ላሸነፊው ዋጋ ውል በመግባትና ክፍያ በመፈጸም በሁለት ወር ጊዜ ውስጠ ባህር ዛፎችን ማንሳት ይኖርበታል፡፡ ይህ ባይሆን ግን ያስያዘው ብር ለመንግስት ገቢ ይሆናል፣
  • ተጫራጮች በራሳቸው ወጪ የባህር ዛፉን ቦታ ማየት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድና ዶክመንታችሁን ኦርጅናሉንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ /ፖስታ/ ሙሉ አድራሻውን በመግለጽ ማህተምና የባለቤቱን ፊርማ በማሳረፍ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀ ጊዜ ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት የባህር ዛፎቹን መጠን የያዘውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በማስያዝ የዕቃዎችን ዝርዝር የያዘውን ሰነድ ከሆስፒታሉ ግዥና ክፍያ ክፍል መረከብ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ፡- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን መጋቢት 24 ቀን 2008 ዓ.ም ከረፋዱ በአራት ሰዓት ተኩል 4፡30 ታሽጎ በአምስት ሰዓት 5፡00 የሚከፈት ስለሆነ በተገለጠው ቀንና ሰዓት ባልተገኘ ነጋዴ ወይም ግለሰብ ምክንያት የጨረታው መክፈት አያስተጓግልም፡፡

መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለበለጠ መረጃ 0913 40 59 12

 

በሰገን አካባቢ ህዝቦች ዞን ጊዶሌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል