Tenders

 

Type: Construction

 

Organization: የከምባታ ጠባሮ ዞን ፋ/ኢ/ል/መምሪያ

Dead Line: 2016-04-16

 

Tender Detail:

 



የከምባታ ጠባሮ ዞን ፋ/ኢ/ል/መምሪያ
የግዥ ክፍያ ንብረት አስ/ር የስራ ሂደት ለዞኑ ውሃ ማዕድን ኢነርጂ መምሪያ የቧንቧ መስመር ዝርጋታና ቭልቭ ቸምበር ግንባታ ለደረጃ 9WWC እና ከዚያ በላይ የሆኑ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በዘርፉ የተሰማራችሁ ሕጋዊ ፈቃድ ያላችሁ ድርጅቶች፡-

  1. የዘመኑን ንግድ ፈቃድ ያሳደሱ፣
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስና የቲን ተመዝጋቢ የሆኑ፣
  3. የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 (አስር ሺህ ብር) ብቻ ማስያዝ የሚችሉ፣
  4. ተጫራቾች አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በተለያየ ፖስታ ማሸግ አለባቸው፣
  5. በፖስታዎቹ ላይ ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ ተብሎ መጻፍ አለበት፣
  6. የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ድረስ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 10.00 /አስር ብር/ ብቻ በመክፈል ሰነዱን ከቢሮ ቁጥረ 25 መግዛት ይኖርባቸዋል፣
  7. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ በ9፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ9፡30 ይከፈታል፣
  8. 16ኛው ቀን ቅዳሜ ዕሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታው ይካሄዳል፣
  9. አሸናፊ ድርጅት ወይም ድርጅቶች አሸናፊነታቸው በተገለጸ በአምስት ቀናት ውስጥ ውል ይፈራረማሉ፡፡

መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- 046 554 00 17

 

የከምባታ ጠምባሮ ዞን ፋ/ኢ/ል/መምሪያ የግዥ ፋ/ን/አስ/ር የስራ ሂደት