Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: የሆሳዕና ከተማ አስ/ር ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት

Dead Line: 2016-04-10

 

Tender Detail:

 



የሆሳዕና ከተማ አስ/ር ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
የከተማ ሴክተር መ/ቤቶች የጥጉ ሰራተኞች የ2008  ዓ.ም ደንብ ልብስ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሰረት፡-

  1. የወንድ ኮት፣ ሱሪና፣ ሸሚዝ ከነስፌቱ፣
  2. የሴቶች ኮት ሱሪና ሸሚዝ /ጉርድ ከነስፌቱ፣
  3. ቱታና ጋዋን፣
  4. ጫማ በንጹ ቆዳ የተሰራ ሲሆን በጨረታ መወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች ማሟላት ያለባቸው ነገሮች፣
  5. የጨመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ምስክር ወረቀት፣
  6. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣
  7. ቢቻል በዚህ ስራ ተሰማርተው የተሻለ አፈፃፀም መኖሩን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
  8. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዱን ከሆሳዕና ከተማ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ግዥ ኬዝ ቲም ቢሮ ቁጥር 14 መውሰድ ይችላሉ፣
  9. ተጫራቾች በባንክ የተመሰከረ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ሲፒኦ በር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ የመጫረቻ ሰነድ በፖስታ በሰም በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
  10.  ጨረታ በ16ኛ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

ማሳሰቢያ፡-

  • የጨረታው አሸናፊ ዕቃውን እስከ ቢሮ ማድረስ ይኖርበታል፣
  • እስከ ቦታው መጥተው የሰራተኛን መጠን መለካት ይኖርበታል፣
  • ዕቃው ውል በገባው በ1 ወር ውስጥ ማስረከብ ይኖርበታል፣
  • በስፌት ላይ የሚከሰተውን ችግር አሸናፊው ድርጅት ኃላፊነት ይወስዳል፡፡

መ/ቤቱ ለጨራው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልና በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለበለጠ መረጃ 046 555 18 41

 

በሐድያ ዞን የሆሳዕና ከተማ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት