Tenders

 

Type: Building Materials

 

Organization: የጎርቼ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት

Dead Line: 2016-04-06

 

Tender Detail:

 



የጎርቼ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት በሰሩ ለሚገኙ ት/ቤቶች የግንባታ ዕቃን ቆርቆሮ፣ ሲሚንቶ እና የተለያዩ መጠን ያላቸውን ሚስማር ገዝቶ ለማከፋፈል ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ፡-

  1. ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የ2008 ዓ.ም ፍቃድ ያሳደሱ ሆነው የአቅራቢነት የምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው፣
  2. የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚችል፣
  3. የጨረታው ዝርዝር መረጃ የያዘ ዶክመንት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበተ ቀን አንስቶ በ7 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 20.00 /ሃያ ብር/ በጎርቼ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት በመክፈል ከጎርቼ ወረዳ ፋይናንስ የጨረታ ሰነድ መረከብ ይችላል፣
  4. የጨረታውን ሰነድ ኦርጂናልና ኮፒ በፖስታ በማሸግ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ በማድረግና ህጋዊ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በ8ኛው የስራ ቀን በጎርቼ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው ሳጥን ከቀኑ 5፡00 እስከ 6፡00 ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፣
  5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በሌሉበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይከፈታል፣
  6. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

 

በሲዳማ ዞን ጎርቼ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት