Tenders

 

Type: Machinary

 

Organization: ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

Dead Line: 2016-04-22

 

Tender Detail:

 





የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ለቀድሞው ብራሌ እርሻ ልማት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሰጥቶት ለነበረው ብድር በዕዳ ማካካሻነት የተረከበውንና ሲያስተዳድረው የቆየውን የእርሻ ልማት ድርጅት ልማት ድርጅት የተለያዩ ቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረቶች እና በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የሚገኘውን የጥጥ መዳመጫ ማሽን ባለበት ሁኔታ በጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 138,317,279.16 /አንድ መቶ ሰላሳ ስምንት ሚሊዮን ሦስት መቶ አስራ ሰባት ሺህ ሁለት መቶ ሰባ ዘጠኝ ብር ከአስራ ስድስት ሳንቲም/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

1. የእርሻ ልማቱ አድራሻ

በደቡብ ብሔር በሔረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት በደቡብ ኦሞ ዞን ሐመር በና ፀማይ ወረዳ እንጨቶና ዱማ ቀበሌ ገበሬ ማህበር የሚገኝ ሲሆን ይህም ከአዲስ አበባ 665 ኪ.ሜ ከአርባ ምንጭ 170 ኪ.ሜ እና ከጂንካ 90 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ ከዋናው አስፋልት አጠገብ ይገኛል፡፡

2. የእርሻ ልማቱ የሊዝ ዘመን

ከደቡብ ኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስ ጋር ለ50 ዓመት የሚቆይ የሊዝ ውል ያለው ሲሆን ይኸውም ከ1987 እስከ 2037 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን የኪራዩም መጠን በዓመት ለሄክታር ብር 30 ነው፡፡

3. የእርሻ ልማቱ አጠቃላይ ሁኔታ

  • የመሬቱ አቀማመጥ ሜዳማ ስለሆነ ለእርሻ ሜካናይዜሽን ምቹ ከመሆኑም በላይ የቆዳ ስፋቱ 5,490 ሄክታር /አምስት ሺ አራት መቶ ዘጠና/ ሆኖ በኩታ ገጠም የሚገኘውም ተጨማሪ መሬት በተመሳሳይ ሁኔታ ለልማት ምቹ በመሆኑ የልማቱን ስራ በስፋት ለማከናወን ከፍተኛ ዕድል ይሰጣል፡፡
  • ወደ የትኛውም የእርሻው ክፍል በማንኛውም አይነት ተሸከርካሪ ለመጓጓዝ የሚያስችል ከአንድ መቶ ኪሎ ሜትር በላይ የውስጥ መንገድ አለው፡፡
  • የእርሻ ልማቱ ከባህ ወለል በላይ ከ520-560 ሜትር ከፍታ ላይ የሚገኝ ሲሆን ዝቅተኛው የሙቀት መጠን 160c ሲሆን ከፍተኛው 300c  የሚርስ ሞቃታማ ነው፡፡
  • የአርሻ ልማቱ ዓመታዊ አማካይ የዝናብ መጠን 557 ሚ.ሜ ሲሆን አማካይ የአየር እርጥበቱ /Relative Humidity/ ከ60% እስከ 80% ይደርሳል፡፡
  • የእርሻ ስራ ለማከናወን የሚያስፈልገውን የሰው ኃይል በተፈለገው ዓይነት እና መጠን ያለምንም ውጣ ውረድ በቅርበትና በቀላሉ ማግኘት የሚቻልበት ነው፡፡
  • የእርሻ መሬቱ የእርሻ ስራ ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የኮንስትራክሽን መሳሪያዎችና የመስኖ መሰረተ ልማቶች ያሟላና በወይጦ ወንዝ ላይ የተጠለፈው ትልቅ ካናል ከራሱ አልፎ የአካባቢውን አርብቶ አደርና አርሶ አደር ህዝብ የሚያገለግል የውሃ ፍሰት ያለው ሲሆን ለቆላ ሰብሎች ምርት እጅግ ተስማሚ የሆነ የተፈጥሮ ምቹነት አለው፡፡

4. እርሻ ልማቱ የሚያለማቸው ዋና ዋና ሰብሎች 

  • ጥጥ፣ ሰሊጥ፣ አኩሪአተር፣ ቦሎቄ፣ የቤት መጥረጊያ /broom com/ ሸንኮራ አገዳ እና የተለያዩ የቆላ ሰብሎች እንዲሁም አትክልትና ፍራፍሬዎች ናቸው፡፡

5. አሁን የሚገኝበት የልማት ደረጃ

  • ለተለያዩ አገልግሎቶች ከዋለው መሬት ውጪ አብዛኛው ሄክታር የመስኖ መሰረተ ልማት ተዘርግቶለታል፡፡
  • ዓመታዊ ጥጥ ምርት መጠን በአማካይ ከ100,000.00 ኩንታል በላይ ደርሷል፡፡ 
  • የራሱ የሆነ የአውሮፕላን ማረፊያ እና መንደርደሪያ አለው፡፡         
  • የኤሌክትሪክም ሆነ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ያለው ነው፡፡

6. በእርሻ ልማቱ ለሃራጅ የቀረቡት ንብረቶች

  • 5,490 ሄክታር የእርሻ መሬት ሲሆን ከዚህ ውስጠ ከ4,000 ሄክታር በላይ የሚሆነው የለማ እርሻ መሬት ነው፡፡
  • በእርሻ ልማቱ ላይ የሰፈሩ ልዩ ልዩ ህንፃዎች ማለትም ቢሮዎች የእንግዳ ማረፊያ ቤቶች /Guest Houses/ በተለያዩ እርከን ደረጃ የሚገኙ ሰራተኞች መኖሪያ ካምፖች፣ ክሊኒክ፣ ጋራዥ፣ መጋዘኖች እና ሌሎችም በርካታ ግንባታዎች፣
  • በእርሻ ልማቱ ላይ የሚገኙ የተለያዩ የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች፣ ዶዘር 3 (ሦስት)፣ ኤክስካቬተር 1 (አንድ) በሙሉ CAT Brand ናቸው፡፡
  • 3 እስካኒያ ገልባጭ መኪናዎች፣ 2 የውሃና የነዳጅ ቦቴዎች (682N3)፣ የወርክሾፕ መሳሪያዎች፣ ግዙፍ ጀነሬተሮች፣ የተለያዩ ቦታዎች ላይ የተተከሉ የነዳጅ ማደያዎች እና ሌሎች በእርሻ ልማቱ ላይ የሚገኙ የተለያዩ ንብረቶች ሲሆኑ በscrap መልክ የሚወገዱ እና ከአገልግሎት ውጪ የሆኑ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን አይጨምርም፡፡  

7. በአዲስ አበባ ከተማ ለሀራጅ የቀረበው ንብረት የቀድሞ ብራሌ እርሻ ልማት ኃ/የተ/የግ/ማህበር ጥጥ መዳመጫ ማሽን ብቻ

  • የጥጥ መዳመጫው ሉሙስ ኢምፔሪያል /Lummus Imperial / ሞዴል 700 የተሰኘ አሜሪካ ሰራሽ ዘመናዊ መሳሪያ ሲሆን በ24 ሰዓት እስከ 150 ቶን / Theoretical capacity/ ጥሬ ጥጥ የመዳመጥ አቅም አለው፡፡

ማሳሰቢያ     

  1. የእርሻውን አጠቃላይ ሁኔታ በግንባር ማየት ለሚፈልጉ ተጫራቾች ባንኩ የጉብኝት ፕሮግራም እንደ አስፈላጊነቱ ሊያዘጋጅ ይችላል፡፡
  2. በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የሚገኘውን የጥጥ መዳመጫ ማሽን በቦታው በመገኘት ከመጋቢት 15 ቀን 2008  ዓ.ም እስከ ሚያዝያ 12 ቀን 2008 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት መመልከት ይቻላል፡፡
  3. የእርሻውን አጠቃላይ ሁኔታ የሚያሳይ የፎቶ አልበም ሳሪስ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ንፋስ ስልክ ቅርንጫፍ በሚገኝበት ህንፃ 3ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 314 ባንኩ በዕዳ ማካካሻነት የተረከባቸው ንብረቶች አስተዳደር ክፍል በግንባር ቀርበው መመልከት ይችላሉ፡፡
  4. ማንኛውም ተጫራች ሌሎች ተጫራቾች በሰጡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋውን 25 (ሃያ አምስት በመቶ ማለትም ብር 34,580,000.00 /ሰላሳ አራት ሚሊዮን አምስት መቶ ሰማንያ ሺህ ብር ብቻ/ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ ክፍያ ማዘዣ /CPO/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስም በማሰራት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. በጨረታው አሸናፊ ሆኖ በብድር ለሚገዛ ተጫራች ባንኩ ባለው የብድር ፖሊሲና መመሪያ መሰረት ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል፡፡
  7. የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች እና ተሽከርካሪዎች ከቀረጥ ነፃ የገቡ ስለሆኑ አሸናፊ ሆኖ የሚገዛ ተጫራች ወደ አገር ውስጥ ለገባለት አላማ እስካዋለ ድረስ ከቀረጥ ነፃ መብት ተጠቃሚ ይሆናል፡፡
  8. ለጨረታ ከቀረቡት ንብረቶች መካከል ምንም አይነት ንብረት ተነጥሎ አይሸጥም፡፡
  9. በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘውን የጥጥ መዳመጫ ማሽን በተመለከተ የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ማሸነፉ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ባሉት ሁለተ ወራት ውስጥ በራሱ ባለሙያና ወጪ ማሽኖቹን አስነቅሎ / Dismantle/ አድርጎ ማንሳት የሚጠበቅበት ሲሆነ ከዛ በላይ ላለ ጊዜ ባንኩ የሚወስንበትን የጥበቃ፣ የኪራይ እና ሌሎች ተዛማጅ ወጪዎችን ይከፍላል፡፡
  10. በሽያጭ ገንዘብ ላይ የሚታሰብ 15% VAT ገዢ ጨምሮ ይከፍላል፡፡
  11. ጨረታው ሚያዝያ 13 ቀን 2008 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋት 4፡00 ሰዓት ላይ ሳሪስ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ንፋስ ስልክ ቅርንጫፍ በሚገኝበት ህንፃ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 314 ባንኩ በዕዳ ማካካሻነት የተረከባቸው ንብረቶች አስተዳደር ክፍል ይከናወናል፡፡
  12. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0114 40 01 55/ 0114 43 08 67, 0114 43 05 92 ወይም 0911 482914 በመደወል ወይም ሳሪስ የኢትዮጵያ ንግደ ባንክ ንፋስ ስልክ ቅርንጫፍ በሚገኝበት ህንፃ 3ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 306 እና 314 ባንኩ በዕዳ ማካካሻነት የተረከባቸው ንብረቶች አስተዳደር ክፍል በግንባር ቀርቦ መጠየቅ ይቻላል፡፡
  13. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ