Tenders

 

Type: Construction

 

Organization: ከሀዋሳ ከተማ ማዘጋጃ ቤት

Dead Line: 2016-02-05

 

Tender Detail:

 

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማ/መምሪያ ከሀዋሳ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የግንባታ ዕቃዎችን፣ የግንብ ድንጋይ፣ አሸዋ ጥራቱን የጠበቀ፣ ጠጠር (02A)፣ የኮብልስቶን ድንጋይ 10x10x10 ሳ.ሜ የሆነውና የትራፊክ ምልክቶች አንፀባራቂ አለም አቀፍ ስታንዳርድ የሆነ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ ልምድ ያላቸው ድርጅቶች እና ማህበራት፣
  2. ተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣
  3. በሥራ ዘርፉ ህጋዊ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ ህጋዊ የሰውነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ማቅተብ የሚችሉ፣
  4. የ2008 ዓ.ም የታደሰ ፍቃዳቸውን ማቅረብ የሚችሉ፣
  5. በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 50/ሃምሳ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10/አስር/ ተከታታይ ቀናት ከፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 03 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፣
  6. ተጫራቾች CPO ከአጠቃላይ ዋጋ 1% ማቅረብ ይኖርበታል፣
  7. ተጫራቾች የተጠየቁ የግንባታ ዕቃዎችን ማቅረብ የሚችሉበት የቦታ ሁኔታ ከሀዋሳ ከተማ ቢያንስ ከ95 ኪ/ሜ ባልበለጠ ርቀት መሆን አለበት፣
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒ በመለየት አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ እያንዳንዳቸው በሰም በታሸገ ፖስታ አድርገው ይህ የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10/በአሥረኛው/ ቀን ከጠዋቱ 5 እስከ 6 ሰዓት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ እንዲሁም የበዓል ቀን ከሆነ የጨረታ ማስገቢያ ቀን በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡ ዐረታው የሚከፈተው በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡
  9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉበሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

            ለተጨማሪ መረጃ 09462215312/0462200665 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡