Tenders

 

Type: Construction

 

Organization: ከሀዋሳ ከተማ ማዘጋጃ ቤት

Dead Line: 2016-02-05

 

Tender Detail:

 

ለሀዋሳ ከተማ ወጣቶች ስፖርት መምሪያ የስታዲዬም ግቢ ንጣፍ፣ የፍሳሽ ማጠራቀሚያ (Septic Tank) እና የውሃ ታንከር ማስቀመጫ ግንባታ ሥራ ለማካሄድ በመስኩ የተሰማሩ ልምድ ያላቸውን ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ቀጥሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ሥራ ተቋራጮች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በኮንስትራክሽን ሥራ ዘርፍ የተሰማሩ ደረጃ BC-6፣ GC-7 እና ከዚያ በላይ ያላቸው፣

  2. በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ የተቋራጭነት ብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

  3. ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣

  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 1% ከባንክ ሲ.ፒ.ኦ ብቻ ማቅረብ ይኖችባቸዋል፣

  5. የጨረታ ሰነዱ ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21/ሃያ አንድ/ ተከታታይ ቀናት ብር 200/ሁለት መቶ ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡

  6. ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦርጅናልና ሁለታ ፎቶ ኮፒ/ቴክኒካል እና ፋይናንሻል/ በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡30-6፡00 ሰዓት በፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 6 ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

  7. ጨረታው በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዎ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 6 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው ሰኞ ጨረታው የሚገባበትና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል፡፡ የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው ሥራ ቀን ይከፈታል፡፡

  8. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

                         ለተጨማሪ መረጃ 0462209963/0462200665

                            ፋክስ ቁጥር፡- 0462208532 ፖ.ሣ.ቁ 02