Tenders

 

Type: Computer

 

Organization: በኦሮሚያ ክልል የሻሸመኔ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

Dead Line: 2015-02-05

 

Tender Detail:

 

በኦሮሚያ ክልል የሻሸመኔ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት፣ አሪሲ ነገሌ ከተማ ውሃ አገልግሎትና በባቱ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት አብሮ በመሆን የተለያዩ ሶፍትዌሮችን ማስጫን ይፈልጋል፡፡

  1. የሶፍትዌር አይነቶች የተቀናጀ የቢል ሶፍትዌር፣ በሞባይል የቆጣሪ ማንበቢያ ሶፍትዌር፣ የሰው ሀይል አስተዳደር ሶፍትዌር፣ የንብረት አያያዝ ሶፈትዌር፣ መረጃ መፈለጊያ እና SMS አገልግሎት ሶፍትዌር፣

  2. በተራ ቁጥር አንድ(1)፣ የተዘረዘሩትን የሶፍትዌር አይነቶች አዘጋጅቶ ለባለሙያዎች ማሰልጠን የሚችል፣

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ህጋዊ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችል፣

  2. ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣

  3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን የሞሉትን ጠቅላላ ቃጋ ድምር 1% በሲፒኦ ለጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ አለባቸው፣

  4. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት የውል ማስከበሪያ የሚሆን የሞላውን ጠቅላላ ዋጋ ድምር 10% ቢድ ቦንድ ከባንክ ወይም ከኢንሹራንስ ማስያዝ አለበት፣

  5. ከአሁን በፊት ከአምስት በላይ የሥራ እና የመልካም ሥራ አፈጻጸም የምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣

  6. የሚዙትን ሰነድ ዋጋ ሞልተው በሚያመጡት ሰነድ ላይ በግልጽ የድርጅቱ ማህተም እና ፊርማ ማድረግ የሚችል፣

  7. ለሁለት ዓመት ዋስትና መስጠት የሚችል፣

  8. ስራውን በሦስት ወር ውስጥ አጠናቆ ማስረከብ የሚችል፣

  9. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 በመክፈል ከሻሸመኔ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት መግዛትና መወዳደር የሚችል፣

የጨረታውን ዋጋ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ሞልቶ ጨረታው በጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስራ አምስት የሥራ ቀናት ውስጥ በፖስታ በማሸግ የሻሸመኔ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የግዥና ፋይናንስ የሥራ ሂደት በመምጣት የግዥ ኦፊሰር ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚችል፣

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 0461 102093/0462 115019