Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: በአማራ ውሃ ስራዎች ኮ/ድርጅት

Dead Line: 2016-05-25

 

Tender Detail:

 





በአማራ ውሃ ስራዎች ኮ/ድርጅት የምስራቅ አማራ ኮ/ጽ/ቤት ያገለገሉ የተለያዩ የውሃ  ፓምፖች፣ ሚክሰሮች፣ ቫይቨሬተሮች፣ በርሜሎች፣ ታጣፊ አልጋዎችና የተለያዩ የኮንስትራክሽን ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሰረት፡-

 

  1. ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡

  2. የጨረታ ሰነዱ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ከፍለው መግዛት ይችላሉ፡፡

  3. ከተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

  4. ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ ደ/ወሎ/ኮቻ ከተማ ቀበሌ 04 በሚገኘው ጽ/ቤታችን መግዛት ይችላሉ፡፡

  5. ተጫራቾች የስልክ ቁጥራቸውንና አድራሻቸውን መግለጽ አለባቸው፡፡

  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በጽ/ቤቱ ስም C.P.O (ሲ.ፒ.ኦ) 10% (አስር ፐርሰንት) በሞሉት ዋጋ መሰረት ማስያዝ አለባቸው፡፡

  7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ሲሞሉ 15% (ቫት) ያጠቃለለ እና ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች አሟልተው በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው፡፡

  8. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 (አስር) የስራ ቀናት ይቆያል፡፡

  9. ጨረታው በ11ኛው (አስራ አንደኛ) ቀን ከጠዋ 3፡30 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በግልጽ ይከፈታል፡፡

  10. ጽቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ዝርዝር መመሪያዎችን በተጫራቾች መመሪያ ሰነድ ላይ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን መረጃ ለማግኘት በስልክ ቁጥር 033 551 09 77 ወይም 033 551 08 48 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

በአማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት

የምስራቅ አማራ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት