Tenders

 

Type: Agricultural Products

 

Organization: የደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት

Dead Line: 2016-05-23

 

Tender Detail:

 





በደቡብ ብ/ብሕ/ክ መንግስት የደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት በመጋዘን ተከማችቶ የሚገኘውን የበቆሎ፣ የሰንዴ፣ የበሎቄ፣ የማሽላ፣ የሰሊጥና የሩዝ የእህል ብጣሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት፡-

  • ተጫራቾች በስራ ዘርፉና ሌሎች ተያያዥ ስራዎች ህጋዊ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸውና የዘመኑን የመንግስት ግብር አጠናቀው ስለመክፈላቸው እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  • የተጨማሪ እሴት (VAT)  የሚመለከተው የቦሎቄ ተጫራቾችን ብቻ ነው፡፡ ተጫራቾች ለጨረታው ውድድር ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የመሰከረለት የክፍያ ማዘዣ (CPO) ማቅረብ አለባቸው፡፡
  • የጨረታው ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 100 በመክፈል በሀዋሳ ከተማ በድርጅቱ ግዥና/ፋ/ንብ/አስተዳደር ክፍል ቢሮ ቁጥር 12 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
  • ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት ውስጥ በሰም በታሸገ ፖስታ /ኤንቨሎፕ/ በማድረግ ኦሪጂናልና ኮፒውን ለየብቻው ከተጓዳኝ ማስረጃዎች ጋር በማደራጅ ሀዋሳ ከተማ በድርጅቱ የግዥ ፋይ/ን/አስ/ክፍል ቢሮ ቁጥር 12 ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በ10ኛው ቀን እስከ 6፡00 ሰዓት ማስገባት አለባቸው፡፡
  • የጨረታው ሳጥን የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ በ8፡00 ሰዓት በተመሳሳይ ሰዓትና ቀን በድርጅቱ የዘር ምርት ዝግጅት ክፍል ቢሮ ቁጥር 8 ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 10ኛው ቀን የስራ ቀን ባይሆን በቀጣይ የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ቦታ ሰዓትና ሁኔታ ይከፈታል፡፡
  • ተጫራቾች የእህሎቹን ናሙና በድርጅቱ መጋዘን ቀርበው ማየት ይችላሉ፡፡
  • ድርጅቱ ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መበቱ የተጠበቀ ነው፡፡

በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሰት የደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት