Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: ወሎ ዩኒቨርሲቲ

Dead Line: 2016-05-28

 

Tender Detail:

 






በወሎ ዩኒቨርሲቲ የኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲዩት ለ2008 ዓ.ም በጀት ዓመት ለመማር ማስተማር አገልግሎት የሚውሉ::

      Lot 1 የደንብ ልብስ /በድጋ የወጣ/

      Lot 2 ኬሚካል እና የተማሪዎች መጠቀሚያ ቁሳቁስ

      Lot 3 ሪዞ የማባዣ ማሽን

      Lot 4 የምግብ ቤት እቃዎች

      Lot 5 የግንባታ ዕቃዎች እና ችፑድ

      Lot 6 ህትመት

በመሆኑም፡-

በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከሎት 1-6 ለተጠቀሱት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን ከወሎ ዩኒቨርሲቲ ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 201 በሚገኘው መውሰድ ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች ከሚያቅቡት ዕቃ ጋር የተዛመደ በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ግብር የከፈሉበት፣ ቫት ገቢ ያደረጉበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

ተጫራቾች ዋጋ መሙላት ያለባቸው ዩኒቨርሲቲው ባቀረበው የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ነው፡፡ እንዲሁም ሰርዝ ድልዝ ያለው የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡

ተጫራቾች ያሸነፏቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ወሎ ዩኒቨርሲቲ ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ማስገባት አለባቸው፡፡

ተወዳዳሪው ላቀረበው ጠቅላላ ዋጋ ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የባንክ ጋራንቲ ብቻ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡

ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ በጨረታው ለተሸነፈ ወዲያውኑ ይመለሳል፡፡

በቀረበው ዝርዝር ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ የሚችል፡፡

አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡

አሸናፊው ድርጅት ያሸነፉቸውን እቃዎች በራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ግቢ ያደርሳል፡፡

ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቱ ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 201 በመገኘት ሰነዱን በመግዛት ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ፖስታውን በማሸግ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት በኮምቦልቻ በሚገኘው የኢንስቲትዩቱ ግዥ ቡድን ቢሮ ጨረታው ይከፈታል የተጫራች አለመኖር ፖስታው ተሟልቶ እስከተገኘ ድረስ ጨረታውን አያስተጓጉልም፡፡

ኢንስቲትዩቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 033 551 03 15 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

በወሎ ዩኒቨርሲቲ

የኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት