Tenders

 

Type: Consultancy

 

Organization: ኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት

Dead Line: 2016-05-28

 

Tender Detail:

 





የኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከዚህ በታች በተመለከተው ኮርስ ላይ ስልጠና ሊሰጡ የሚችሉ ተጋባዥ ኮንሰልታንቶች /አሰልጣኝ/ ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በኢንስቲትዩቱ ቢሮ ተገኝታችሁ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ተ.ቁ

የስልጠና መስክ የኤሌክትሮ ሜካኒካል መሳሪያዎች ጥገና ቴክኖሎጂ ስልጠና

ተፈላጊ ችሎታ

ሎት 1

Generato operation and Maintenance

አመልካቹ ድርጅት ከሆነ በሙያው በማሰልጠን ወይም በተግባር ስራ ላይ የሶስት ዓመት ልምድ

አመልካቹ ግለሰብ ባለሙያ ከሆነ በሙያው 6 ዓመት ማሰልጠን ወይም የተግባር ልምድ ያለው

ሎት 2

Pump set

 

ማሳሰቢያ

  1. ተወዳዳሪዎች በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የትምህርትና የስራ ልምዳቸውን ማቅረብ ይገባቸዋል፡፡
  2. ለስልጠናው የሚጠይቁትን ክፍያ መግለጫ ለብቻው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይገባቸዋል፡፡
  3. የግብር ከፋይነት መለያ  (TIN) ማቅረብ ይገባቸዋል፡፡
  4. ተወዳዳሪዎች የተዘጋጀውን RFP በምዝገባ ወቅት መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 868 61 67 ወይም 011 829 02 15 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አድራሻ

የኢትዪጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በቀለበት መንገድ ከአቦ ቤተክርስቲያን ወደ ማሰልጠኛ ወረድ ብሎ ኖክ ማደያ ሕንፃ ላይ 3ኛ ፎቅ በሚገኘው የግዥ፣ ፋይናንስ፣ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ መመዝገብ የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት