Tenders

 

Type: Autos

 

Organization: የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ

Dead Line: 2016-06-07

 

Tender Detail:

 





አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁ የተሽከርካሪ ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

  1. ተጫራቾች የ2008 ዓ.ም ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሰጠ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዌብሳይት ላይ የተመዘገቡበት እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡

  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) እየከፈሉ አቃቂ ቃሊቲ ወረዳ 09 ቂሊንጦ ከጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል ከፍ ብሎ በሚገኘው የዩኒቨርሲቲው ግቢ ህንፃ ቁጥር 24 ዘወትር በስራ ሰዓት በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

  3. ተጫራቾች የፋይናንሻልና ቴክኒካል ሰነዳቸውን በአንድ ፖስታ በማሸግ የጨረታ ሳጥኑ ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከላይ በተራ ቁጥር 2 ላይ በተመለከተው አድራሻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 10,000.00 (አስር ሺ ብር) በሲፒኦ () ወይም በሁኔታዎች ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከቴክኒካል መወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

  5. ጨረታው ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በእለቱ ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም 4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል፡፡

  6. ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ነው፡፡

  7. ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፤

ስልክ ቁጥር፡- 0118 69 60 94 /0118 69 61 20

አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ቂሊንጦ ቀበሌ ከጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል 3 ኪ.ሜ ገባ ብሎ፣ ከአዲስ አበባ ከተማ በቃሊቲ መስመር መንገድ ወይም በጎሮ መስመር በአዲሱ ቱሉ ዲምቱ ደ/ዘይት መንገድ በቀላሉ መድረስ ይቻላል፡፡

የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ