Tenders

 

Type: Autos

 

Organization: በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት

Dead Line: 2016-06-07

 

Tender Detail:

 





በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት በደቡብ ወሎ ዞን የሚገኙ ያገለገሉ የመኪና ሞተሮችን እና መለዋወጫዎችን በደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር መምሪያና በየፑል በሚገኙ ንብረት ክፍሎች እንዲሁም በደቡብ ወሎ ዞን ባሉት 22 ወረዳዎች ጊዜያዊ ማዕከል በማድረግ ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

  1. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም አካል በጨረታው የመሳተፍ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

  2. ተጫራቾች የንብቶቹን ዓይነት ዝርዝር መግለጫ በጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡

  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50.00 /ሀምሳ ብር/ በመክፈል በደቡብ ወሎ ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 03 ግዥና ንብረት አስተዳደር ከ12/9/2008 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 26/9/2008 ዓ.ም 11፡00 ሰዓት ድረስ የከፈሉበትን ደረሰኝ በመያዝ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡

  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ/ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በመ/ቤቱ የገቢ ደረሰኝ በማስቆረጥ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡

  5. ተጫራቾች ለሽያጭ የቀረቡ ንብረቶችን በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ በተገለፀው ከ12/9/2008 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 26/9/2008 ዓ.ም 11፡00 ሰዓት ድረስ በአካል በመሄድ ማየት ይችላሉ፡፡

  6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን /መጫረቻውን/ ዋናውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአገልግሎት ጊዜያዊ ማዕከል ደቡብ ወሎ ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 01 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ከ12/9/2008 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 29/9/2008 ዓ.ም ጀምሮ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

  7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 01 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡

  8. ተጫራቾች አንድ ወይም ከዚያ በላይ ከተጠቀሱት መለያ ቁጥሮች በተጨማሪ መወዳደር ይችላሉ፡፡

  9. የጨረታው አሸናፊ የሚለየው ለንብረቶች በተሰጠው መለያ ቁጥር መሰረት ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ይሆናል፡፡

  10. ተጫራቾች በአንድ መስሪያ ቤት ለአንድ የንብረት ወይም የእቃ ዓይነት ከተገለፀው መጠን/ብዛት እና መለያ ቁጥር ውስጥ ቀንሶ መወዳደር አይችሉም፡፡

  11. ተጫራቾች በመወዳደሪያ ፖስታቸው ላይ ስም፣ ፊርማ፣ ስልክ ቁጥራቸውንና የተወዳደሩበትን የእቃ ምድብ መፃፍ አለባቸው፡፡

  12. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033 112 3904 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

  13. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት