Tenders

 

Type: Machinary

 

Organization: የጅማ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

Dead Line: 2016-06-18

 

Tender Detail:

 





የጅማ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለሆስፒታሉ ለታካሚዎች ምግብ ማብሰያ አገልግሎት የሚውል የምግብ ማብሰያ የሲሊንደር ጋዝ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት በጨረታ መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ሕጋዊ ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል፡፡

  1. በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልግ ሁሉ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር የእቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ሊስት ላይ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ፣ በዘመኑ ታደሰ አግባብ ያለው የንግድ ፈቃድ፣ የሀገር ውስጥ ገቢ የድጋፍ ደብዳቤ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀትና ግብር ስለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋጋ ሞልተው ሲመልሱ ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 /ሀምሳ ሺህ ብር/ በCPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

  3. ተጫራቾች ላሸነፉባቸው እቃዎች አቅርቦቱን የሚፈጽሙት በራሳቸው የትራንስፖርት ወጪ በጅማ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እቃ ግምጃ ቤት ድረስ በማቅረብ ነው፡፡

  4. ተጫራቾች ማናቸውንም የመንግስት ታክስና የግብር ግዴታዎችን ከነመጓጓዣው በሚያቀርቡት እያንዳንዱ የመወዳደሪያ ነጠላ ዋጋ ውስጥ አካተው ማቅረብ አለባቸው፡፡

  5. ካለይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ማንኛውም ተጫራች ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግዥ ክፍል ቢሮ ማስፈፀሚያ ጽ/ቤት ቢሮ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በግንባር መረጃዎችን ይዞ በመቅረብ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

የጨረታው ሰነድ የሚዘጋውና የሚከፈተው

  1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን እስከ ሰኔ 10 ቀን 2008 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው በጅማ ከተማ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግዥ ክፍል ቢሮ በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው ሰኔ 10 ቀን 2008 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጅማ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

      • የበለጠ መረጃ ቢያስፈልግዎት በስልክ ቁጥር 0472115220/0471110870 ጅማ ወይም 0111550621 አዲስ አበባ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

      • ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የጅማ ዩ/ስ/ሆስፒታል