Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል

Dead Line: 2016-06-18

 

Tender Detail:

 





የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል

  •  ሎት-1 የላውንደሪ እጥበት አገልግሎት
  •  ሎት-2 በሆስፒታሉ ለህሙማን የምግብ አቅርቦት
  •  ሎት-3 በግቢው ውስጥ የሚገኘው የግሪን ኤሪያ ቦታ ማስዋብና

መንከባከብን አውት ሶርስ በማድረግ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን የተጫራቾች መመሪያ ማክበር አለባቸው፡፡

  • በሎት-3 ላይ የተቀመጠውን በግቢው ውስጥ የሚገኘው የግሪን ኤሪያ ቦታ በተለያዩ እጽዋቶች በእሳር፣ በነጠላ ከርቭ ስቶን፣ እንዲሁም መንገዱን በቴራዞንና መከለያ ደግሞ በብረትና በሰንሰለት ተሰርቷል፡፡ በመሆኑም የአረንጓዴ ቦታውን በበለጠ በማስዋብና ባለበት በማስቀጠል የሚንከባከብለት ስለሚፈልግ በሙያው ልምድ ያላቸውን በጥንቃቅንና አነስተኛ የተደራጁትን ሁሉ አወዳድሮ ለማሰራት ስለሚፈልግ
  • ተጫራቾች ከስራው ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያለው ህጋዊ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  • ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከብር 100000.00 /አንድ መቶ ሺ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፡፡
  • ተጫራቾ የመጫረቻ ዋጋ ሰነዳቸውን ዋናውንና የማይመለስ ኮፒውን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ በአየር ላይ ከዋለበት (ከወጣበት) ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከዘውዲቱ መታሰቢ ሆስፒታል ግዢ ክፍል ቀርበው መውሰድ ይችላሉ፡፡
  • ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ እያንዳንዳቸው ገጽ ላይ ማህተም ተደርጎ ኦሪጅናልና የማይመለስ ኮፒውን በመለየት በፖስታ ታሽጎ የአስተዳደር ህንፃ ተደርጎ ኦሪጅናልና የማይመለስ ኮፒውን በመለየት በፖስታ ታሽጎ የአስተዳደር ህንፃ 2ኛ ፎቅ በግዢ ክፍል በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፤
  • ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የሚያሳይ ሰነድ በማይመለስ ብር 50.00 (ሃምሳ) በመክፈል ጋዜጣው በአየር ላይ ከዋለበት ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት በተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ከዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል የአስተዳደር ህንፃ 2ኛ ፎቅ የግዢ ዕ/ዝግ/አፈጻ/ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቀርበው መውሰድ ይችላሉ፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድቦንድ/ ብር ከሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ 10%  በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ስም የተዘጋጀ ማቅረብ አለበት፡፡
  • ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ከቫት ጋር መሆኑን እና አለመሆኑን በግልጽ መለየት አለባቸው፡፡
  • ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ተዘግቶ በዚያው ዕለት ከቀኑ 9፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዢ ዕቅድ ዝግጅት አገልግሎት ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ በጨረታ ቡድኑ ይከፈታል፡፡
  • 10ኛው ቀን በዕረፍት ወይም በበዓል ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  • የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኃላ የሚደርስ ማንኛውም ሰነድ ሳይከፈት ለተጫራቹ ይመለስለታል፡፡
  • ሆስፒታሉ ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

                            ለበለጠ መረጃ፡ በስልክ ቁጥር 011115 02 42 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

                    አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ቂርቆስ ክ/ከተማ ፍል ውሃ አጠገ ገባ ብሎ ይገኛል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል