Tenders

 

Type: Construction

 

Organization: መስሪያ ቤታችን የዲላ መንገድ ዲስትሪክት ጽ/ቤት

Dead Line: 2016-06-25

 

Tender Detail:

 




መስሪያ ቤታችን የዲላ መንገድ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ለዲስትሪክቱ የመንገዶች ግንባታ ፕሮጀክቶችና የመንገድ ጥገና መስመሮች እስትራክቸር ስራዎች አገልግሎት የሚውሉ ቱቦዎች ለማምረት ይረዳው ዘንድ ባለ 6 እና 8 ፌሮ ብረቶችንና ማሰሪያ ሽቦ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሰረት ተወዳዳሪዎች የመወዳደሪያ ሃሳብ እንድታቀርቡ እየጠየቅን መስሪያ ቤታችን ግዢውን የሚፈጽመው በጥራትም ሆነ በዋጋ ብቁ መሆናቸውን አረጋግጦ የመረጣቸውን ነው፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን፡-

  1. የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ በአቅራቢነት የተመዘገቡበት የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የመንግስት መስሪያቤቶች በሚያወጡት ጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የምስክር ወረቀት እና ከሀምሳ ሺህ ብር በላይ ለሆኑ ግዢዎ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የሚያቀርቡት እቃ በኢተዮጵያና በአለም አቀፍ ደረጃ በወጣላቸው መስፈርት መሆን ይኖርበታል፡፡
  3. የመወዳደሪያ ሀሳቡ በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የስራ ቀናት ሆኖ በዚያው እለት እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ እለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
  4. አቅራቢዎች የሚያቀርቡት ዋጋ ጨረታው ከተከፈተ ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት ጸንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል፡፡
  5. የእቃዎቹ የማስረከቢያ ቦታ ዲላ መንገድ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ዲላ ከተማ ሆኖ ግዢው ከታዘዘበት ጊዜ ጀምሮ በሦስት ተከታታይ ቀናት ውስጥ ይሆናል፡፡
  6. አቅራቢዎች ጠቅላላ ዋጋውን በቁጥርና በፊደል መጻፍ አለባቸው፡፡ በቁጥርና በፊደል የተገለፀው የዋጋ መጠን መካከል አለመጣጣም ካለ በፊደል የተገለጸው ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ በነጠላ ዋጋና በጠቅላላ ዋጋ መጠን መካከል ልዩነት ካለ ነጠላ ዋጋው ተቀባይነተ ይኖረዋል፡፡
  7. አቅራቢዎች በእያንዳንዱ የእቃ ዝርዝር ማቅረቢያ ሰንጠረዥ ውስጥ ነጠላ ዋጋውንና ጠቅላላ ዋጋውን እንዲሁም ቀን፣ ፊርማና የድርጅቱን ማህተም ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡
  8. አሸናፊው ተጫራች እቃውን ሙሉ በሙሉ በተፈለገው ጥራት መሰረት አጠናቆ እስከ ዲላ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ማስገባቱ ከተረጋገጠ በኃላ ቢበዛ /ሦስት/ ቀናት ውስጥ ሙሉ ክፍያ ይከፈለዋል፡፡
  9. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን የሚያካትት መሆኑና አለመኖኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል፡፡
  10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡


ተ/ቁ

የእቃው ዓይነት

መለኪያ

ብዛት

የአንዱ ዋጋ ቫትን ጨምሮ

ጠቅላላ ዋጋ

ምርመራ

01

ብረት ፌሮ ባለ Ø8

ኪ.ግ

 

 

 

 

01

ብረት ፌሮ ባለ Ø6

ኪ.ግ

 

 

 

 

02

ማሰሪያ ሽቦ

ኪ.ግ

 

 

 

 

 

                           ማሳሰቢያ፡- የትራንስፖርት ወጪ የሚሸፈነው ከአሸናፊው ድርጅት ይሆናል፡፡