Tenders

 

Type: Agricultural Products

 

Organization: የደ/ብርሃን የበግ ብዜትና ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል

Dead Line: 2016-06-19

 

Tender Detail:

 





የደ/ብርሃን በግ ብዜት እና ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል አገልግሎት የሚውል የተመጣጠነ የበጎች መኖ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም፡-

  • በጨታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች በየዘርፉ አግባብ ያለው በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ከፌዴራል መኖ እንስሳትና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን የብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች በዘርፉ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 10 /አስር ብር/ በመክፈል ከግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ደ/ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 3 በመግዛት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ የካላንደር ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ የሚሸጡበትን ዋጋ በመሙላትና ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒውን በማያያዝ በደ/ብርሃን የበግ ብዜትና ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
  • ጨረታው በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  • ተጫራቾች የሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ ከ50,000 /ከሀምሳ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  • የጨረታ ማስከበሪያ ቫትን ጨምሮ የጠ/ዋጋውን 1 በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  • ተወዳድረው የአሸነፉ ድርጅቶችን ያሸነፉትን ንብረት ማዕከሉ ድረስ አምጥቶ ማስረከብ አለበት፡፡
  • ማዕከሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
  • የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከናወናል፡፡
  • ማዕከሉ ከላይ ለሚፈልጋቸው ግዥዎች በዘርፉ ለሚወዳደሩ ተወዳዳሪዎች የሚያገለግል እስፔስፊኬሽን በጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይቻላል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡ በስልክ ቁጥር 011 681 14 63 እና 011 681 23 30 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የደ/ብርሃን የበግ ብዜትና ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል